17.3 C
Asmara
Wednesday, September 13, 2023

”ሓመድ ኢድሪስ ዓዋተ 1915-1962 ” ታላቁ ኤርትራዊ የታሪክ ቅርስ

ይህ መፀሐፍ በዋናነት የአርበኛው ሓምድ ኢድሪስ ዓዋተ የትግሉን ጉዞ  የሚዳስስ ነው። መፀሐፉን ወደ አንባቢያን  እጅ ለመድረስ የአንድ ወጣት ዕድሜ ያክል ማለትም 35 ዓመታት ነው የፈጀው።

ከዚህ በፊት ከተጻፉት የትግርኛ መጻፀሐት በዓይነቱም ሆነ በይዘቱም ለየት ያለ ነው። ይህ መፀሐፍ በኤርትራ የነጻነት ትግል ጊዜ ተጀምሮ በነጻነት ጊዜ የተጠናቀቀ ነው። በሂደቱ  ደራሲው  የአርበኛውን  ዓዋተ የትግል ጓዶቹን በኣካል ለማግኘት፣ ሃቀኛውን ታሪኽ ለመዘገብ በኢትዮጰያ ሁመራ፡ በሱዳን ከስላና በኤርትራ ቆላማና ደጋማ ቦታዎች በመዘዋወር፣ መረጃና ማስረጃ በማሰባሰብ ሌት ተቀን ለፍቶ ለህትመት ያበቃው የኤርትራ ህዝብ የቅርብ ጊዜ ታሪክ ይሚያወሳ ታሪካዊ መፀሐፍ ነው።

በአንድ በኩል የደራሲውን  ትዕግስትና ፅናት፣ በሌላ በኩል ደግሞ ደራሲው የታሪክ ሃላፊነት ተሸክሞ እንዲህ ዓይነት ጥራት ባለው መልኩ ፅሕፉን ለህትመት በማበቃት አንባብያን እጅ  ላይ ማድረሱ ምስጋና ቢያንሰው አንጂ አይበዛበትም። የታሪኩ ይዘትና የደራሲው አቀራረብ ለአሁኑና ለመጪው ትውልድ አንድ ትልቅ ቅርስ እንደ ገፀ-በረከት እንዳአበረከተ ነው መታየት አለበት። ለዚህም ነው ደራሲውን በሚገባ ማወቅ፣ መረዳተና ማመስገን የሚጠበቅብን። ምስጋና ግን በቂ ስላሆነ መፀሐፉን ገዝቶ በማምበብና  እቤት ወስጥ አንደ ታሪካዊ ቅርስ ማኖር የዜጎች ግዴታ የሚሆነው። ምክንያቱም በአሁኑ ጊዜ የህዝቦችንም ሆነ የሃገራት  ታሪኮች በማንና እንዴት እየደሚጻፉ  ስለምናውቅ። ከዚህ በፊት ስለ እኛ በሌሎች ዜጎች የተጻፈልንን ታሪክ ይብቃ በለን ደራሲዎቻችን ማበረታታት ገዴታችን ነው።

ደራሲው ሃይለስላሴ ወለዱ በ1948 ተወልዶ፡ የአንደኛና ሁለተኛ ደረጃ ትምህርቱን ኤርትራ ውስጥ ካጠናቀቀ በሃላ፡ ኣዲሰ ኣበባ ዩኒቨርሲቲ በመግባት በመምህራን ማሰልጠኛ ኢንስቲቱት የአንድ ዓመት ትምህርቱን አጠናቀቀ። ከ1970-1973 በጋምቤላ እንደ አስተማሪ፡ በኢትዮጵያ አየር መንገድ እንደ ጸሃፊ በመሆን ሰርተዋል። ከ1973-1975 በኤርትራ ሃገራዊ ጉዳይ ትንቀሳቀሳለህ ተበሎ ”አለም በቃኝ ” ወህኒ-ቤት ታሰረ። በ1976 ከኤርትራ ታጋዮቸ (ህዝባዊ ሓይልታት) በመቀላቀል እሰከ 1982 በተዋጊ ሰራዊት፡ ከ1983-1992 በዜና ሚኒስትርና በመገናኛ ሚኒስትር በተለያዩ የስራ መሰኮች ሰርተዋል።

ይህ መፀሐፍ የአርበኛውን ሓምድ ኢድሪስ ዓዋተ ታሪክ ከልጅነት እስከ መስዋእት የሚተነትን ታሪካዊ ሰነድ ሲሆን፣ ኣብሮውት ከነበሩ የትግል ጓዶቹና ለታሪኩ ቅርበት ካላቸው ሰዎች ጋር በተደረገ ቃለ-መጠየቅና የዛን ዘመን ሰነዶችን በማሰባሰብ የተሰራ ድንቅ የሆነ ይዘት ያለው ታሪካዊ መፀሐፍ ከመሆኑም ባሻገር ከዚህ በፊት የነበሩትን ታሪካዊ ብዥታዎችንም በደምብ ያጠራ ትልቅ ኤርትራዊ ቅርስ ነው።

ሓመድ ኢድሪስ ዓዋተ በ1915 በሃበራዳ ሞጎራይብ በሚባል ቦታ ተወለዶ በእርሻ ይተዳደር እንደነበር፣ በ1935 ከጣልያን ጋር በውትድርና ተቀጠሮ እንደነበረ፣ ከ1940-1941 ደግሞ በሱዳን ከስላ በጸጥታ ኣስከባሪነት ተመድቦ ይሰራ እንደነበረና የ2ኛ ዓለም ጦርነት ሲያበቃ ወደ ሃገሩ እንደተመለሰ ይነገራል። ሓመድ ኢድሪስ ዓዋተ በ1951 በኤርትራ የእንግሊዝ ኣስተዳደር ያወጣውን የምህረት ኣዋጅ ተቀብሎ ወደሃገሩ ከተመለሰ ብኃላ፣ በፈደረሽኑ ጊዜ በአንዳን ሃይሎች ይመራ የነበረውን ኤርትራን ከኢትዮጵያ ጋር የማዋሃድ እንቅስቃሴ ኣጥብቆ በመቃወም በ1961 የትጥቅ ትግል ለመጀመር ይመጀመርያዋን ጥይት በመተኮስ የነፃነት ትግሉን አቀጣጠለው።

በመጨረሻም ደራሲው ካሳውን የሚከፈለው መፀሐፉን በመግዛትና በማንበብ ስለሆነ፣ ይህ የደራሲው እድሜን የበላ መጽሓፍ  በእያንዳንዱ ኤርትራዊ ቤት ማኖር ትልቅ የታሪክ ቅርስ እንደማሰቀመጥ ይቆጠራል። ምክንያቱም ከላይ እንደተገለጸው ደራሲው 475 ገጽ የያዘ መፀሐፉን ታሪካዊ ኃላፊነት በመሽከም እንደ እህል የሚበላ፡ እንደ ውሃ የሚጠጣና  በሕውሳት የሚዳስስ ትልቅ የታሪክ ሠነድ ስላቀረበልን።

ይህ አሁን  ” ዝክሪ ባሕቲ መስከረም ” እያልን ከ1961 ጀምሮ ላለፉት 60 ዓመታት መሰከረም 1 የሚከበረው የነፃነት ትግል የጀመረበት ቀን ከሓመድ ኢድሪስ ዓዋተ ጋር በእጀጉ የተቆራኘ ታሪከ ሰለሆነ፡ መፀሐፉን መግዛት፣ ማንበብና በክብር የተከበረ ቦታ ላይ ማስቅመጥ የግድ ይላል፣ ምክንያቱም ኤርትራዊ ታሪክ ክቡር ቅርስ ነውና።

Must read

ጅግንነት ኤርትራውያንን ኢትዮጵያውያንን ኣብ 50 ዓመቱ

ዓርቢ 08 ታሕሳስ 1972፡ ቅድሚ 50 ዓመት፡ ኣብ መዓርፎ ነፈርቲ ኣዲስ ኣበባ ሓደ ምንጋሩ ዘጸግም ፍጻሜ ተኻየደ። ኣብ ክሊ ዕድመ 24- 28 ዝርከቡ ሰለስተ ኤርትራውያንን ኣርባዕተ ኢትዮጵያውያንን ንነፋሪት ንመገዲ ኣየር ክጨውዩ ተበገሱ። እቶም ክልተ ተማሃሮ ዩኒቨርሲቲ፡ እቶም ኣርባዕተ ገሊኦም ትምህርቶም ዛዚሞም ኣብ ስራሕ ዝተዋፈሩ...

ናጽነት ከቢድ ዋጋ ከፊልካ ይመጽእ፣ ከቢድ ዋጋ እንዳኸፈልካ ድማ ይዕቀብ

"ዝሞተ ነይክሰስ ኣብ ሰማይ ነይሕረስ" እኳ እንተኾነ፣ ስቕ ዘየብል ክትዕዘብ እንከለኻ ስቕታ ኣይትመርጽን። "ኣዲኣ ገዲፋስ ሓትንኣ ትናፍቕ" ከምዝብሃል ብምኽንያት ሞት ንግስቲ ዓባይ ብርጣንያ ልዕልቲ ኤልሳቤጥ፣ መንግስቲ ኬንያ ናይ ሰለስተ መዓልታት ሃገራዊ ሓዘን ኣዊጁ ክትስምዕ ዘደንጹው እዩ። መቸም ብሰንኪ ምስፍሕፋሕን ጎበጣን ንግስነት ዓባይ ብርጣንያ ኣብ ሃገራትን...

ሓንጎል፡ ሓሞት፡ ደም

ኣብዚ ቀረባ ቕነ ንሓጺር እዋን ምስቲ ኣዝየ ዘድንቖ መራሒ ተራኺበ ከዕልል ዕድል ረኺበ ነይረ።  ምልክት ቃልሲ ኤርትራውያን ንናጽነትን ኣርካን ኣቦ ሰውራን ውሩይ መራሒ እዩ። ብትሑት ኣነባብራኡን ምቕሉልነቱን ዝፍለጥ ሰብ እዩ። ኣብ መዓልታዊ ህይወቱ ዝገብሮ ንጥፈታት ካብ ዝኾነ ተራ ዜጋ ዝተፈልየ ኣይኮነን። ከም ተራ ዜጋ ይኽደን፡ ኣብ መንጎ ህዝቡ ኣብ ንእሽቶ ገዛ ይነብር፡ ከምቲ ልምዲ ሕብረተሰብና ድማ ኣብ ኩሉ ማሕበራዊ ንጥፈታት ከም ዝኾነ ተራ ዜጋ ይሳተፍ። ኣብ መላእ ሃገር ብናጽነት ዝንቀሳቐስ፡ ምስ ህዝቡ ሕዉስ መራሒ...

Shida Friendship Forum

On the occasion of Eritrea’s 31st Independence Celebrations, Shida Media will live stream a panel discussion on Saturday 21st of May at 9AM LA time, 12PM NY time, 6PM Berlin time and 7PM Asmara and Addis Ababa time. The distinguished panelists are: Alemseged Tesfai -...

More articles

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

- Advertisement -spot_img

እዋናዊ ዜና