ልዘመናት ሃገራትን በመጨቆንና በመዝረፍ ህዝቦችን በተለያዩ መንገዶች በመጉዳት ላይ የተመሰረተ የጥቅም ሰንሰለት የገነቡት ሃገሮች እያስቸገሩን ነው።
በአፍሪካው ቀንድ የለመዱትን ዝርፊያና ሽበራ ለማስቆም በቁርጠኝነት ለረዦም ጊዜ ትግሉን ይመራችው ኤርትራን ለማፍረስ ያልሰሩት ሴራና ያላንኳኩት በር የለም። ህዝቦችን በማጋጨት የሃገራትን ንብረት ዘራፊ ሃገሮች: አፍሪካን ተመጽዋች እነርሱ ደግሞ መጽዋቾች አድርገው ፖለቲካውን ቀርፀውታል።
እርዳታ መስጠት እንፈልጋልን ነገር ግን እኛ ያልናችሁን ባለመስማታቹሁ እርዳታችንን አቁመነዋል እያሉ ነው። ለመሆኑ ማንው ተረጂው?
ኤርትራ መዝባሪ ስርአታቸውን ኣላስተናግድም አሻፈረኝ ብላ ናላቸውን አዙራዋለች። አሁን ደግሞ ኢትዮጵያ ተጨምራበት ወደ እብደት እያመሩ ነው። በታሪክ የተረጋገጠ ሃቅ አለ። የነርሱን እርዳታን የወሰድ በሙሉ ከሞትና ብጥብጥ በስተቀር አንድም እድገት ያሳየችው ሃገር የለም።
ስለ ጥቅማቸው እንጂ ስለ ሰብአዊ መብቶች አስበውም ይሁን ገብቷቸው አያውቅም።
እንነጋገር ከተባለ ከ90 ሺ በላይ ኤርትራውያን ንብረታቸው ተዘርፎ ከመላው ኢትዮጲያ በግፍ ሲባረሩ አንዲትም እንኳን ትንፍሽ ኣላሉም።
እሱ ይቅርና ትናንትና በመቶዎች የሚቆጠር ኑጽሃን በማይ ካድራው ዘር ማጥፋት ጭፍጨፋ ሲገደሉ፣ በአስመሳይ ሞራላቸው የሚመሩት ተቋሞቻቸው ልሳናቸው ምነው ተዘጋ?
ለ27 ዓመታት የነርሱ ስራ አስፈጻሚው አውሬ እራሱ በለኮሰው እሳት ስለተበላባችው በቂም በቀልና በኩርፊያ ተነድተው ያሰብነውን እርዳታ ኣቁመናል ኣንሰጥም ቢሉ ኣይገርመንም።
ሲጀምር ተረጂዎች እንጂ ረጂዎች ሆነው አያውቁም!
አካባቢው እራስን መስሎ መሄድን የጀመረ ይመስላ። አስመሳዮቹም በደምብ እስኪዋጥላቸውና እስኪቀበሉትድረስ ረብሻ ማስነሳትና ሽብር መንዛታቸውን እንደሚቀጥሉ እርግጥ ነው።