16.7 C
Asmara
Saturday, November 27, 2021

ሰንደቅ-ዓላማው ሲተከል

በኤርትራ ሰማያት ስር ያልታለመ ክፋት፣ ያልተሰራ በደል፣ ያልተፈጸም ግፍ፣ ያልተተኮሰ የጦር መሳሪያ የለም።
የኤርትራ ህዝብ በሰላም ወዳድነቱና በእንግዳ ተቀባይነቱ የሚታወቅ፣ ትጉህና ታታሪ ህዝብ በመሆኑ፣ በእንግድነት
ተቀብሎ ያላስተናገዳቸው የኣካባቢው ህዝቦች የሉም ብንል የተጋነነ ኣይሆንም። የኤርትራ ህዝብ በእንግድነት ከተቀበላቸው
ህዝቦች፣ ገሚሶቹ ህዝቡንና ሃገሩን መስለው ለዘመናት ከህዝቡ ጋር በመኖር በሂደት ኤርትራውያን ተላበሱ። ገሚሶቹ ግን የህዝቡን መልካምነትና የዋህነት አንደ ሞኝነት በመቁጠር፣ ልክ ከእሾህ ጋር እንደተጠጋች ኣጋም ለዘመና ሲያቆስሉት ቆይተዋል።
በዚህ የዘመናት ሂደት፣ የኤርትራ ህዝብ በጣም ኣሰልቺ እና እልህ ኣስጨራሽ ትግሎችን ኣልፎ፣ ብዙ መስዋእቶችን ከፍሎ ኣሁን የምናያትን ጠንካራና የኣፍሪካ ተምሳሌት ለመሆን የምትበቃ ሃገረ ኤርትራን ለመትከል በቃ።

እንደ ኣውሮጳውያን ኣቆጣጠር ከ 1961 እስከ 1991 ዓ ም በተደረገው የነጻነት ትገል፣ ትግሉን ይመራ የነበረው ህግሓኤ ከዘር፣ ከሃይማኖትና ከብሄር ነጻ የሆነ፣ በኣንድ የልብ ህርመት የሚራመድ ኤርትራዊ ማንነትን መገባት ቻለ። ከሁሉ በላይ ግን በራሱ የመተማመን፣ ሃገሩን በስራ መቀየር እንደሚችል የሚያምን፣ ለወሬና ኣሉባልታ ጊዜ የማይሰጥ፣ ተመጽዋችነትን ይሚጸየፍ ዜጋ መኮስኮሱ ልቡዙ ጭቁን ህዝቦች መሳሌ ሲሆን፥ ለተቀሩት መዝባሪ ቡርዝዋዎች ደግሞ ራስምታት ሆኖባቸው ቆይቷል።

ኤርትራዊያን አርስ በርሳቸው ”ደቂ ሓደ ልቢ” (የአንድ ልብ ልጆች) በመባባል ይግባባል፡፡ በፍቅር ኣና በሰላም ከጎረበቶቻቸው ጋር ለመኖር እና ለመስራትም ሁሌም ዝግጁ ናቸው። የኤርትራ መንግስት በትእግስቱና በዝምታው የሚትወቅ ሲሆን፣ የዝምታው ጥበብ ተገማች እንዳይሆንና ለብዙ ፖለቲካዊ ጉዳይ ቢጠቅመውም፡ በምዕራቡ ዓለም ህብረተሰብ ዘንድ ግን የህ ዝምታው እንደ ዲፕሎማሲ ስራ ጉድለቶች ተቖጥሮ ነጋ ጠባ የጋዜናዎቻቸው ርእሰ-ዓንቅጾች ወግ ኣድርገውታል፡፡

ለነገሩ ሲወራ ቢዋል የትኛውን ግድብ ተሰርቶ ውሃ ሊይዝልን? የትኛውን አስፋልት ተዘርግቶ መንገድ የሆናን?
የትኛውን እርሻ ለምቶ ዘር የሰጣል? የህን በመገንዘ ይመስላ የኤርትራ መንግስት ዝምታን የመረጠው።

ቴክኖሎጂ ሰማይ ጥግ በደረሰበት ዘመን: ዓለም በአንዲት ጠባብ መስኮት ተሰብስባ አፍ ለአፍ ገጥማ ስታወጋ በምትውልበት ዘመን፣ ምንጩ ያልተረጋገጠ ዜና በቅጽበት በሚሰራጪበት በዚህ ዘመን፣ እውነት ከሃሰት መለየት ኣስቸጋሪ የሆነበት ሁነታ ተፈጥሯል፡፡ ያልተፈጠሩንና ያልሆኑ ነገሮች እንደተፈጸሙ ክውንነቶች ኩሎ በማቅረብና በፍጥነት ሰው ጆሮ ውስጥ መሰካት፤ በሃሰት ህዝብን ከህዝብ ማጋጨት፤ መሪዎችን ማጠልሸት፤ በግብር ከተሸነፉ በወሬና በውሸት ማስረጃ አገር አለሙን ማመስ የመሳሰሉትን እኩይ ተግባራት በአጭር ግዜ ለማራባት ብዙ ስራ የማይጠይቅ ዘመን ሆኗል፡፡

የኤርትራ ህዝብ ላለፉት 80 ዓመታት የምዕራብ ሓይሎችን በሎለነት በሚያገለግሉ በጎረበት ሃገራት መንግስታት በተሰነዘሩባት ጦርነቶች፥ ሃገሩን በጦር ምሳሪያውች ሺያጋዩበት፣ ህዝቡን በመድፍ፣ በታንክና፣ በናፓል ቦምብ ሲያነዱት፤ የዲፕሎማሲ ተነጥሎ ጫናና የተቀነባበረ የሃሰት ፕሮፓጋንዳ ጥቃቶችን ተቓቁሞ፥ 30 ዓመታት የፈጀ ረጅምና ውስብስብ ትግል ኣካሂዶ ሰንደቅ-ዓላማውን ለመትከል የበቃ ሰላማዊ ህዝብ በመሆኑ ኩራት ሊሰማው ይገባል።

ኤርትራ የከፈለቻቸው እነዛ ቁመናቸው የሚያማልል ወጣቶች፡ ኮረብታ ላይ ሰንዳቅ-ዓላማቸውን ከፍ ኣድርገው ሲተክሉ፣ ፎቶውን ለሚታዘበው ሰው ምናልባትም በድሎት የሚኖሩ እስካውቶች ሊመስሉት የችሉ የሆናል። ዛላቸውና ቅርጻቸው የተሸከሙትን የሃገር እዳ ደብቆላቸው፤ ያለፉትን ሰቆቃ ሽሮላቸው እንደ ዋዛ ጀርባቸውን ሰጥተው የተከሏት የምትመስለው ሰንዳቅ-ዓላማ፣ የብዙ ዘመናት የግፍ ቀንበርን ቀብራና የብዙ ወጣቶችን ደም ጠይቃ ነው በኩራት ደረቷን ወድራ ከፍ ያለችው፡፡

ዛሬ ኤርትራ 30ኛውን የነጻነት በዓላን ስታከብርና፣ ለ30ኛ ጊዜ የሚታሰበው የሰማእታት ቀንን ለብሳና ተንተርሳ ነው። የህን የክብር ካባ ላልበሱን፣ ኤርትራዊነትን በአንድ ህርመት አጣምረው ለተሰዉት ጀግኖቻችንን የምናስታውስበትና ይምናስብበት: ቃለ-ማሓላችንን በድጋሚ የምናድስበት ግዜም ነው፡፡ ላለፉት 20 ዓመታት ኤርትራ እንዳትለማና እንዳንበልጽግ ተጭኗት የነበረውን ጠፍር በጣጥሳ የምትመኘውን ብልጽግና የምታይበት ዘመን ጀምሯል፡፡

ከሁሉም በላይ በምዕራባዊያን የሚመራውና ለሆዳቸው ያደሩ ረዝራዦችን በመሳሪያነት እየተጠቀመ በተቀናጀ መልኩ የሚቃጣውን ባዶሽ የሃሰት ፕሮፖጋንዳ ፊት ለፊት ገጥመን: የኤርትራን ነጻነት ዋጋ የምናስተምርበትና የምናሳይበት ምዕራፍ ነው፡፡ በድል የተወጣነውን ድምቀታችንን በትህትና ማስረዳት እንደሆን አያቅተን።

Must read

”ሓመድ ኢድሪስ ዓዋተ 1915 -1962 ” ዓቢ ኤርትራዊ ናይ ታሪኽ ቅርሲ

እዚ መጽሓፍ ብቐንዱ ናይ ሓርበኛ ሓምድ ኢድሪስ ዓዋተ ናይ ቃልሱ ጉዕዞ ዝድህስስ እዩ። እዚ መጽሓፍ ናብ ኢድ ኣንበብቲ ንኽበጽሕ ዕድመ ሓደ መንእሰይ ማለት 35 ዓመታት ዝወሰደ ዓቢ ናይ ድርሰት ስራሕ እዩ። እዚ መጽሓፍ ካብቶም ቅድሚ ሕጂ ዝተደርሱ ናይ ትግርኛ መጻሕፍቲ በዓይነቱ ይኹን ብትሕዝቶኡ ፍልይ...

ድጉል ወያነ “ትንሽ ኣሻሮ ይዘህ ከቆሎ ተጠጋ”

“ትንሽ ኣሻሮ ይዘህ ከቆሎ ተጠጋ” እዛ ኣበሃህላ ንኣኻ ንኣረጋዊ በርሀ ብትኽክል ትገልጽ ኮይና ረኺበያ ኣለኹ። ከብርሃልካ ኢየ፥ ሰዓበኒ። ንስኻ ብወያነ ተረፊትካ ኣብ ስደት ኣብ ዝተቐመጥካሉ ነዊሕ ዓመታት ብዘይካ ውልቃዊ ዋኒንካ እዚ ኢልካ ክትጠቕሶ ዝከኣል ጸረ ወያነ ቃልሲ ከምዘይገበርካ ብዙሓት ዝፈልጥዎ ጉዳይ ኢዩ። እንተኾነ ግን ኣብ ኢትዮጵያ ዝመጸ፡...

እታ ዕብዲ/ጽልልቲ ሓኪም

ንምኒስከርታ ክትንክፍ ዘው ዝበለ ሃሪ መሳሊ ነዊሕ ጸጉራ እናወዛወዘት ብትምህርታን ማሕበራዊ ናብራኣን ዝመቀረ ሂወት ዝነብራ ሓኪም፣ ንሳ ዝኸደቶ ጫፍ መን ይግምቶ?  እዛ ብደም-ግብኣታ ሰላቢት ዝኾነት መንእሰይ፣ ዕድላ ካኣ፣ ሰብ ዝዕዘቡ ከምዝመስሉ ዉቅባት የዒንታ ኩሉ ዝጸበቐ'ዩ ነይሩ። ንላዕለዋይ ደረጃ ትምህርቲ ናይ ነጻ ትምህርቲ ዕድል ዝረኽበቶ ኣብ...

መጽሓፍ ንምግዛእሲ ክንድዚ ወጠጥ!

ነዚ ክጽሕፍ ዘበገሰኒ፣ ኣብ ሓደ ናይ ስነጥበብ መደብ 5 መጻሕፍቲ ኣብ ቅድሚ'ቲ ደራሲ ብ11 ሽሕ ብር (4 በብ 2 ሽሕ 1 ብ3 ሽሕ) ክሽየጣ ምስ ረኣኹ እየ። እቲ ዝያዳ ዘደነቐኒ ካኣ እቲ ነተን 5 መጻሕፍቲ ብጨረታ ንምግዛእ ኣብቲ ዕዱም ዝነበረ ምቅድዳም እዩ። እዚ ነቲ...

More articles

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

- Advertisement -spot_img

እዋናዊ ዜና