19 C
Asmara
Wednesday, September 13, 2023

ኣሜሪካ በኢትዮጵያ ላይ እንዴት እና ለምን ዛሬ?

ይህ ኣሁን በኢትዮጵያ ህዝብና ኣገር ላይ የሚያንዠብበውን ጥቁር ደበና ኣይቼ ካሁን በፊት “ኢትዮጵያ ለምን ይሆን” በሚል ርእስ በሂወት ዘመኔ የሰማሁትን ሳይሆን ያየሁትን ለመመስከር ሞክሬ ነበር። ኣስተያየት ኣቅራቢው በሃይለስላሴ ዘመን መንግስት በኢትዮጵያ በትግራይ ጠቅላይ ግዛት ብ1948 ዓ.ም ትውልደ ኤርትራ ከሆኑ ቤተሰብ ነበር የተወለድኩት።

ኣባቴ የዝያን ዘመን የጦር ሰራዊት መኮነን ስለነበር እሱ ለስራ ከቦታ ቦታ ሲዘዋወር ቤተሰቡ ኣብረነው እንጓዝ ስለነበርን በብዙ ኣካባቢዎች ከኢትዮጵያ ህዝብና መልክኣ ምድርዋ ጋር 19 ዓመት እስኪሞላኝ የማወቁን እድል ኣግኝቻለሁ። በዚህ መሃል ኣንድ እማልረሳው ገጠመኝ ትዝ ይለኛል። እኔ የ12ኛ ክፍል መልቀቅያ ብሄራዊ ፈተና ለማለፍ ሌተ ቀን ደፋ ቀና ስል ዘውዳዊ ኣገዛዙ በኢትዮጵያ ህዝብ ላይ ያደርስ የነበረው ግፍና በደል ህዝቡ ከሚችለው በላይ ስለሆነበት በሁሉም ኣቅጣጫ የሞት ሽረት ትግል በማቀጣጠል ላይ ነበር። እኔና የክፍል ጓዶቼ የ12 ክፍል መልቀቅያ ፈተና ለመውሰድ በዝግጅት ላይ እያለን ፈተና እምንወስድበት ቀን ለ3 ግዜ ማለት ከሚያዝያ ወደ ግንቦት ብሎም ወደ ሰኔ 1966 ዓ.ም ሲገፋ ቆይቶ በሰኔ ወር ወሰድን። እኔና መሰሎቼ ፈተናውን እንዳለፍን ከተነገርን በኋላ ክረምቱን የሃይለስላሴ መጻኢ በመከታተል ላይ ነበርን። ህዝቡ የመልካም ኣስተዳደር፣ የዲሞክራሲ፣ የባላባትና ጭሰኛው የተዛባ ዝምድና ወዘተ ላይ ያተኮረ ፈተና ኣዘጋጅቶ በመከላከያ ሰራዊቱ ታዛቢነት ወደ 4 ኪሎው የፈተና ኣደራሽ የገባው ሃይለስላሴ ግን ማለፍ ቀርቶ ወድቆ የስብርባሬው ደበዛ እስኪጠፋ ሆነ። ታዛቢ ሆኖ ሁኔታውን በቅርብ ይከታተል የነበረው መከላከያ የስልጣን ክፍተቱን ያለ ምንም ተወዳዳሪ ወድያውኖ ኮረቻው ላይ ቖጢጥ ኣለ።

በጊዜው የነበሩትን ከፍተኛ ባለስልጣናትና የረጅም ግዜ ወታደራዊ ልምድ የነበራቸውን ጀነራሎች ኣንድ በኣንድ ለቅሞ “በፍየል ወጠጤ” ሽለላ ወደ ማይመለሱበት ኣለም ኣሰናበታቸው። ከሞት የተረፉትን በሃምሳ ኣለቃ እሚመሩ ባለ 5 ኮኮብ ጀነራሎች የያዘች ኣገር መዳረሻዋ የት ይሁን? የሚል ጥያቄ በማንኛውም ኢትዮጵያዊ ይነሳ ነበር።

ሆኖም ግን ህብረተሰባዊት (ሶሻሊስት) ኢትዮጵያ እመሰርታለሁ የሚል መፈክር በማንሳት ደርግ የህዝብ ወገንተኝነቱን ለማሳየት ሞከረ። የህዝቡን ልብ ይሰልባሉ ያላቸውን ሓቀኛ ምስሎች በተቆጣጠራቸው መገናኛ ብዙሃን ማሳየትና ማስማት ተያያዘው። በተለይ ያኔ ይቀርቡ ከነበሩት ቀዳሜውን ቦታ የያዘው ለተደጋጋሚ ኣመታት እሚላስ እሚቀመስ ስለኣጣው የወሎና የትግራይ ህዝብና ያስከተለው ዘግናኝ እልቂት ነበር። ለመከላከያ ሃይሉም ለተወሰነ ግዜ ተቀባይነት የማግኘት እድል ሰጠው። በተለይ ሞት ምን መሆኑን የማያውቅ የወራት ህጻን ልጅ የሞተች እናቱን ጡት ነክሶ ሲመጥ የታየው ህጻን ኢትዮጵያንና ህዝቧን ብቻ ሳይሆን ኣለምን ከዳር እስከዳር የደም እንባ ኣስለቀሰ። እኔም ይህን ትርኢት በጥላሁን ገሰሰ “ዋይ ዋይ ሲሉ የረሃብን ጉንፋን ሲስሉ” በሚለው ዘፈን ታጅቦ ሳይ በዚህ መጣ ያላልኩት እንባ ፊቴን ኣጥቦ ከኣንገት በታች ያለውን ሸሚዜን እንዳበስበሰው ትርኢቱ ኣልቆ ወደየቤታችን ስንሄድ ነበር ያየሁት።

ብዙ ሳይቆይ ግን ተማሪው “ህዝባዊ መንግስት ይቁም” ሰራዊቱ ወደ ካምፑ ይመለስ እሚሉ ወታደራዊ ስርዓቱን እንቅልፍ እሚነሱ ጥያቄዎች ይዞ ብቅ ብቅ ኣለ። የዚህ ህመም ኣስተላላፊ ቫይረስ ያላቸውን ከሁለተኛ ደረጃ ትም/ቤት በላይ ዩኒቨርሲቲንና የሞያ ኮለጃትን ጨምሮ ወደ እድገት በህብረት የእውቀትና የስራ ዘመቻ ያለ ምንም ጥናትና ዝግጅት በተነን። እኔም እንደ ማንኛውም የጊዜው ተማሪ ወደ ኢሊባቡር ጠ/ግዛት ቡኑ በደሌ ኣውራጃ ያዩ ወረዳ ዘመትኩ። ኣጭር እድሜ የነበራቸው የፖለቲካ ድርጅቶች ኢህኣፓና መኢሶን ዲሞክራሲ እና ሰፊው ህዝብ የሚባሉ በራሪ ጽሁፋቸውን በድብቅ እየበተኑ ትግሉን ማቀጣጠል ላይ ይሰሩ እንደነበር ትዝ ይለኛል።

ደርግ ብልጣ ብልጥ ነኝ ብሎ በሁሉም የጠቅላይ ግዛት ወረዳዎች የበተነው ተማሪ ህዝባዊ ኣመጹን በኣጭር ጊዜ በሁሉም ኣካባቢ እንዲዳረስ ደርግ ራሱ ሁኔታውን ኣመቻቸ። “ኣተርፍ ባይ ኣጉዳይ” ይሉችሃል እንዲህ ነው። በሌላ በኩል ደርግ መኢሶን፣ ሰደድ ወዘተ እሚባሉትን ድርጅቶች ኣቅፎ ኢህኣፓን ማሳደድ የቀን ተቀን ስራው ሆነ። ስፍር ቁጥር የሌለው ተማሪ ኣለቀ። ጥቁር ልብስ ለብሰው ደረታቸውን እሚደበድቡና ጠጉራቸው እሚነጩ ልጆቻቸው በኣረሜኔው ደርግ የተነጠቁ እናቶች ቁጥርም የዝያኑ ያህል ነበር። ባልና ልጅ፣ ሁለት ሶስት ልጆቻቸውን ያጡ እናቶች ቁጥርም ቀላል ኣልነበረም። እኔ በነበርኩበት ወረዳ ላይም “ግዛቸው” የተባለ ከወይዘሮ ስሂን ሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት ደሴ የመጣና በኣዲስ ኣበባ መምህራን ማሰልጠኛ ኮተቤ በኩል የዘመተ ስራ ውለን ስንመለስ የወረዳው ፓሊስ ባለባቶችን ኣስተባብሮ በከፈተብን ተኩስ ሂወቱን ኣጣ። ያኔ በወረዳችን የኢህኣፓ ኣባልና ወኪል የነበረው ኋላ ግን በከሃዲው ቡዱን የጀነራል ማእርግ የለበሰና የኢትዮጵያ ኣየር ሃይል ኣዛዥ የነበረው ኣበበ ተክለሃይማኖት በቅጽል ስሙ ጀቤና ዑስማን ተብሎ የሚጠራ እዛው እኛጋ ነበር።

ከኣዲስኣበባ ዩኒቨርሲቲ ኣራት ኪሎ ሳይንስ ፋካሊቲ እንደመጣም ኣስታውሳለሁ። የዚህ ወንድማችን ሞት ተከትሎ ወረዳው ላይ የነበርነው ዘማቾች ለደህንነታችን ተብሎ ለጊዜው ወደ በደሌ ወሰዱን። የደርግ ከፍተኛ ባለስልጣናት በሻለቃ ሲሳይ ሃብቴ እሚመሩ ኣራት “የለውጥ ሃዋርያት” በሚል ቅጽል ስም እሚጠሩ መጡና ለስብሰባ ተቀመጥን። ሽጉጥ ከታጠቁ ሃዋርያት ምን ኣዲስ ነገር እንዳይገኝ እያለ ዘማቹ ጓዴ በስብሰባው ኣዳራሽ ቦታ ቦታውን ያዘ። ስብሰባው ተጀምሮ ገና ኣንድ ሁለት ጥያቄ እንደቀረበላቸው የዛቻና ፎከራ ቋታቸው ተፈታ ። ድንፋታው ኣያድርስ ነው። እናት ኣገራችን በሰሜን በፔትሮ ዶላር ቅጥረኞች፡ በምስራቅ በሶማሊና በኣጠቃላይ በምእራቡ ኣለም የሚቃጣባትን በትር በመመከት ላይ እያለች፡ እናንተ እንዴት የተመደባችሁበትን ጣብያ ለቃችሁ መጣችሁ።ኣሁን ኣሁን በኣጭር ግዜ ወደ ጣብያችሁ ተመለሱ፡ካልሆነ ግን ኣብዮታዊ ስይፋችን ይመዘዝባችኋል ተባልን። በዚህ ግዜ ነበር እኔ ያኔ ባስባስብኩት ጥራዝ ነጠቅ የፓለቲካ ኣቅሜ ደርግን በመፈክርና ሰላማዊ ሰልፍ ብቻ መጣል እንደማይቻል የገባኝ። ዘማቹ ጓዴ ከደርጎች ፎከራና ዛቻ በኋላ ሻንጣውን ጠቅሎ ወደ ወረዳው ተመለሰ። እኔ ግን ኣሁን በሂወት ይኖሩ ኣይኖሩ ኣላውቅም፣ ከ10 በሃሳብ ከሚግባቡኝ የወረዳው ዘማቾች ጋር ሆኜ ኣዲስ ኣበባ ገባን። ልጆቹ ከደሴ ሲሂን ትምህርት ቤትና ከሓረር ድሬ የመጡ ናቸው። በሂወት እስካለሁ የማይፋቅ ትዝታ ትተውልኛል። ለጥቂት ግዜ ኣዲስ ኣበባ ኣራት ኪሎ ኣከባቢ ጥዋት ጥዋት እየተገናኘን ተወያያን። እመጨረሻ ላይ ግን በየ ኣከባብያችን ወደ ኣሉ ታጣቂዎች ገብተን ለመታገል ተስማምተን ተለያየን።

የኔ ጉዞ ከሁሉም የራቀና ውስብስብ እንደሚሆን ስለገመቱ 100 (መቶ) ብር ኣዋጥተው ሰጡኝ። 100 ብር ያኔ 50 US ዶላር ነው። ምክንያቱም 1 US ዶላር በ2.10 ብር ይመነዘር ስለነበር በጣም ብዙ ነው። ስንለያይ ይህን በህዝቦቻችን ፊት የተጋረጠውን እሹህ ኣሜኬላ ጠራርገን በነጻነት ለመገናኘት ያብቃን ብለን ተማምለን ተሰነባበትን። እኔ ነጻነት ፍለጋ ኣዲስ ኣበባን ትቼ በረርኩ። ያኔ ገና ጨቅላ ወደ ነበረው ተሓህት ተቀላቀልኩ። እነሱጋ ስቀላቀል እኔን ጨምሮ በቁጥር 50 ነበርን። በኣንድ ኣመት ቆይታየ ብዙ ለመስማት እሚዘገንን የፈጠራ ታሪክና የትግራይ ሪፓብሊክ መንግስት ምስራታ ጨምሮ ሌሎች ደስ እማይሉኝ ስሜቶችን ኣነበብኩ። በተለይ እኔን ከሁሉም በላይ ስሜቴን የነካው ቸጉቤራን adventurer የሚል ቅጽል ስም ሲሰጡት ስሰማ ወደ ትውልድ ኣገሬ የምሄድበትን መንገድ ፍለጋ ላይ ሌተ ቀን ሰራሁ። በመጨረሻ በህጋዊ መንገድ ትውልድ ኣገሬ ወደሚገኘው ሻዕብያን ለመቀላቀል ኣስናበቱኝ።

ምንም እንኳ በቀጣዮ ኣመታት 4 ግዜ በጥይት 10 ግዜ ደግሞ በእጅና መድፍ ቦምብ ፍንጣሬ ኣካላቴ ቢሰነጣጠቅ ይህው ዛሬም ኣለሁ። በ15 ዓመታት ከሻዕብአያ ጋር ቆይታየ ያሳለፍኩት የወንድማማችነት፣ የፍቅር፣ የደስታና ኣንዱ የሌላውን ሂወት ለማትረፍ ይደረግ የነበረውን እሽቅድድም ሳስታውስ ደግሞ ብሂወቴ ይህን ኣይነት ዕድል ዳግም ኣገኝ ይሆን ብየ ራሴን በራሴ እጠይቃታለሁ። ከኣዲስ ኣበባ ባስ ትኬትን ቆርጠው ያሰነበቱኝን ወሎየዎችንና የድሬ ልጆችን ሳስታውስ ውለታቸውን ባለመክፈሌ ይጸጽተኛል ግን ደግሞ ተማምለን የተለያየንበትን ነጻነት ከምወደውና ከማከብረው ህዝብጋ ሆኘ እዉን በማድረጌ እጽናናለሁ።

ገጠመኞቼ ጥር 16-1948 እለተ ኪዳነ ምህረት ትግራይ ተወልጄ ጎንደር፣ ጎጃም፣ ኢሊባቡር ሽዋን ትግራይንና ኣገሬ ኤርትራን ከዳር እስከዳር ኣዳርሼ ግንቦት 16-1983 ኪዳነ ምህረት ኣስመራ በነጻነት መግባቴና፣ ሌላው በጣም ኣስገራሚና ምስቅልቅል ገጠመኝ፦ እኔ ወያኔን ተቀላቅየ ትግራይ ዓሲምባ ላይ ሁላችንም የዚያኑ ግዜ ታጋዮች ተሰብስበን ከመረጥናቸው 8 ኣመራሮች፣ 3ቱ በዚህ የከሃዲ ቡዱን የስልጣን ብልግና ሳይጨማለቁ እዛው በትግሉ ወቅት መሰዋታቸው፣ 2 ከሃዲውን በግዜ ተገንዝበው ጥለውት የሄዱና፣ ኣሁን የለውጥ ኣመራሩ ባደረገው ጥሪ እህዝባቸው መሃል ሆነው ኣዲስ ኣበባ መገኘታቸውና፣ ኣንዱ የኣባይ ግድብ እርዳታ ኣስተባባሪ ሆኖ ማየቴ፣ 2ቱ ለ27 ዓመት ሲንከባለል የቆየውን ጥጋባቸውን መቻል ተስኖኣቸው በሰሜን እዝ ላይ በከፈቱት ጦርነት ሞተው መገኘታቸውና፣ ኣንድ የመጨረሻው ግን ውጭ ኣገር እንዳለ መስማቴ ኣግራሞቴን ሰማይ ሰቀለው። ዕድሜ ከሰጠኝ ስለነዚህ 8ቱና ተከታዮቹ የወያኔ ኣመራሮች የማውቀውን ለማካፈል ቃል እገባለሁ።

ውድ ኣንባቢያን መነሻ ርእሱን ኣልዘነጋሁትም ግን ለመረጥኩት ርእሰ ጉዳይ ከየት ተነስቼና እንዴት የሚከተለውን ለማለት እንደበቃሁ ከላይ የጠቃቀስኩትን እንደ መግቢያ ማለት ግድ ስለሆነብኝ ነው። በሉ እንግዲህ ስለ ዲሞክራትዋ ኣሜሪካና ለሰይጣናዊ ተልእኮ፣ ስለምትቀጥራቸው ተላላኪዎች በሂወት ዘመኔ ያየሁትን እንካችሁ።

  1. ከኣያት ቅድመ ኣያቶቸ ዲሞክራስን የወረስኩና ተተርፍርፎብኝ ከስንዴው እኩል ዲሞክራሲ ለኣለም ህዝቦች በእርዳታ የምለግሰው ቀዳሜዋ እኔ ነኝ ብላ ስትኩራራብን የቆየችውና ያለችው ኣሜሪካ ናት። ብዙ ሩቅ ሳንሄድ ግን የነበረው የኣምናው ፕሬዚደንት በምርጫ ተወዳድሮ ኣሁን ባለው ሲሸነፍ ያየነው ውጣ ውረድ፣ ግድያና ውድመት ቀጥሎም ተሸናፊው ኣኩርፎ ኣዲስ ለተመረጠው ፕሬዚደንት ስልጣኑን በኣግባብ ሳያስረክብ ወደ ትውልድ መንደሩ መፈርጠጡ የምን ምልክት ነው? እነሱ ራሳቸው ማድረግ ያልቻሉትን ሌሎችን በእዚህ ውጡ በዚህ ውረዱ ማለቱ ከቅን ልቦና የመነጨ የህዝቦችን ችግር ለመፍታት ነው ወይስ እነሱ በፈለጉት መንገድ ለረገጣ ማመቻቸት? ሌላው የቅርብ ግዜ ፍጻሜ ነጭ ኣሜሪካዊ ፓሊስ የጥቁር ኣሜሪካዊውን ዜጋ ኣንገት ረግጦ ኣሰቃይቶ መግደሉስ የዘር ልዩነት እማይታይባት ዜጎች በእኩልነት እሚነሩባት ኣገር ኣለችን ለማለት ድፍረቱም ሞራሉም ይኖራቸው ይሆን?
  2. ከሃይለስላሴ እስከ ኢህኣደግ ህዝብን ደም ያስለቅሱ የነበሩትን ኣመራር እሽርሩ እያለ ሲያቀማጥልና ለህዝብ ረገጣ የሚውል የጦር መሳርያና ስልጠና ሲስጥ የቆየው የኣሜሪካ መንግስት ነው። ኣሁን ግን የህዝባቸውን ብሶት እሚስሙና ለመፍትሔ ሌተ ቀን በሚሰሩ ባለስልጣናት ላይ እገዳ መጣል የኢትዮጵያ ህዝብ ስለተበደለ ነው ወይስ በቅጥረኛው ወያኔ ላይ በተወሰደው እርምጃ የፈሰሰውን ደም ለመበቀል።ሃይለስላሴ በስልጣን እያለ በሰሜን ኢትዮጵያ ወሎና ትግራይ ላይ ለ4 ዓመታት የቀጠለው ድርቅና ያስከተለው ኣሰቃቂ እልቂት ያየሁትን ላካፍላችሁ። መቀሌ – ኣዲስ ኣበባ መንገድ ላይ እሚመላለሱ ሹፌሮች የተራበው ህዝብ መንገድ ዘግቶ ኣላሳልፍ ይላቸው ነበር። ይህን ያስተዋሉ ሽፌሮች በግራ ጎናቸው ዳቦ የሞላ ሳኬት ይዘው ጉዞኣቸውን ይጀምራሉ። መንገድ እንደጀመርን እዚህም እዛም በኣወራ ጎደናው ግራ ቀኝ የተንጋለለው ህዝብ የመኪና ድምጽ ሲሰማ ኣውራ ጎደናውን ይዘጋል።

    ይህኔ ሽፌሩ በግራ ጎኑ ያለውን መስተዋት ከፍቶ 5 እሚሆኑ ዳቦ ይወረውራል። መንገዱን የዘጋው ህዝብ እነዚህን ዳቦ ለማግኘት ሲሽቀዳደም ኣውቶቡሱ ፈትለክ ብሎ ጉዞዉን ይቀጥላል። እንዲህ እንዲህ ብለን ወልድያ ለምሳ ስንቆም በሁሉም ምግብ ቤቶች በራፍና መስኮት ከቦ ህዝቡ ያሳይ የነበረው ትርምስ ለመግለጹ ይከብዳል። በዚህ ተመሳሳይ ጊዜ በኤርትራ “እምቢ ያለ ሰው ጥይት ኣጉርስው” ኤርትራ መሬቷ እንጂ ህዝቧ ኣያስፈልገንም ብሎ የሃይለስላሴ ሰራዊት እየዘመረ ምዕራባዊና ምስራቃዊ ቆላ ኣከባቢ ከሚገኙ የገጠር መንደሮች እንደነ ዓይለት ጉምሁት፣ ዓዲ ዑመር፣ ዑና፣ ፍረዳርብ ቤትጁራ፣ ዓዲ ኢብሪሂም ሕርጊጎና ሌሉችን ከደጋማው ከባቢ ሃዘሞ፣ ወኪ ዱባ፣ ወኪ ዛግር፣ በለዛ፣ እምባደርሆ፣ ኳዜንና በሌሎች ብዙ የገጠር መንደሮች የሚገኝ ህዝባችንን በኣብያተ ክርስትያናትና መስጊድ ሰብስቦ በእሳት ኣጋየ። እያንዳንዳቸው ከ1000 እስከ 3000 ንጹሃን ዜጎችን ኣቅፈው የነበሩ መንደሮች እንዳሉ ወደሙ። ይህ ኣልበቃ ብሎት ሰራዊቱ ለመግባት ያልደፈራቸውን መንደሮች በF-5 ና F-86 ከኣሜሪካ በተለገሱ የጦር ኣውሮፕላን 5 ኩንታል በሚመዘን ቦምብና ሰፊ ቦታ ለማቃጠል ተብሎ በተሰራ ክላስተር ቦምብ መሸሽ እማይችሉትን ኣረጋውያን፣ እናት ኣባቶቻችንና ህጻናት ወንድም እህቶቻችንን በሺዎች እሚቆጠሩ ለሞት ዳርጓል። ዝርዝሩን ግፍዕታት ተብሎ ሕድሪ ያሳተመውና፣ ጃንሆይና ደርግ ተብሎ በተስፋይ ገብረኣብ የተተረጎመውን መጽሓፍ ማየት ይቻላል። ከዚያን ዘመን እስከ ትላንት የኢህኣደግ መንግስት ዘመኑ ያፈራቸውን ኣዳዲስ ከምድር፣ ከባህርና ከኣየር የሚተኮስና የሚተኩሱ መሳሪያዎች ስታተጥቅ ስትለግስ እንጂ፣ ትራክተርና ምርጥ ዘር ስትለግስ ኣላየንም። ታድያ እንዴትና ለምን ይሆን ኣሁን የኢትዮጵያ ህዝብ ከረጅም ታሪኩ ብዙ ልምድ ኣካብቶ ከኣብራኩ በወጡ የቁርጥ ቀን ልጆቹ ድህነትን ለመቅረፍ ተፈጥሮ ኣገሪቱን የለገሰላትን ለም መሬትና ከራስዋ ኣልፎ ጎረቤት ኣገሮች የሚያጥለቀልቅ ወንዞችዋን በጥቅም ላይ ስታውል እገዳ መጣሉ ምስጢሩ ምን ይሆን? እንደኔ ምስጢሩ ግልጽ ነው። ካሁን በፊት የስልጣን ዕድሜያቸውን ለማራዘም እሚጥሩ ተላላኪ መንግስታት ስለነበሩና ኣሁን ግን በሰጡት የኖቬል ሽልማትና በገቡለት ቃል ሳይደናገር የኣገሩንና የህዝቡን ጥቅም የሚያቀድም መንግስት ስላለ ነው።

  1. ኣሜሪካ በኣለማችን በተለያዩ ኣከባቢዎች ከእገዳ እስከ ወታደራዊ ጣልቃ ገብነት ማካሄድ የታሪኳ ኣንዱ ምስሶ ነው። ሶርያ፣ ኢራቕ፣ ኣፍጋኒስታን፣ ሊብያ የመንና ፍልስጤም ወዘተ ብሎብዙ መጥቀስ ይቻላል። ከቅርብ ኣመታት በፊት በሶማሌ ሞክራ ቀድመው ኣፍንጫዋን ስለሰበራት ግን ፈትለክ ብላ መፈርጠጥዋንና ስው ኣልባ የጦር ኣውሮፕላን ኣርጋ መቀጠልዋን ሁላችንም በእኔ እድሜ ክልል የምንገኝ የዚህ ከባቢ ህዝቦች የቅርብ ጊዜ ትዝታችን ነው። ኣሜሪካ ቀን የጣለው ወታደር ሲማርክባት ወይ ስለያዎችዋ በሌላ ሞያ እንደተሰማሩ ሆኖው ለምሳሌ፦ እንደ ጋዜጠኛ፣ የረድኤት ሰራተኛ ወዘተ መስለው የቆዩ ሲያዙባት ለማስፈታት የማትከፍለው የገንዘብ መጠን፣ የማትለቃቸው በቁጥጥርዋ ስር የቆዩ እስረኛና የማታደርገው ዲፕሎማስያዊ ጫና ብዙ ማስረጃ ማቅረብ ይቻላል። የዚህ ተቀጥያ ነው ኣሁን በቅርብ ጊዜ ሞቱ በመቃብር ኣፋፍ ላይ ያለውን ወያኔ ለማትረፍ ላይ ታች ስትል ለማየት የበቃነው። በራሱ ኣቅም የማይተማመነው ወያኔ ኢትዮጵያን ተቆጣጥሮ በኣጠቃላይ የዚህን ከባቢ ሃገራት ለማተራመስና የኣሜሪካን ፍላጎት ለማስፈጸም ቅጥራኛ ሆኖ መቆየቱን ድንግርግር ሲለን የቆየነውን የዋሆች ይብቃችሁ ተብለናል። ጊዜ ደግ ነው፡ ቀጣሪውንና ተቀጣሪውን ሸፋፍኖ የነበረውን ኮበርታ ገላልጦ እርቃናቸውን ኣሳየን።
  2. ከለውጡ ማግስት የለውጥ ሃይሉ ወንጀለኞችን ወደ ሕግ ማቅረብ ሲጀምር ወያኔ ፈርጥጦ መቀሌ መወሸቁን የማያቅ ኢትዮጵያዊ የለም። የኣሲምባው ኣራዳ በ6ኛው ሃገራዊ ምርጫ ለመወዳደር በወጣው መስፈርት ቁመናችሁ ኣይመጥንም ተብለው የተባረሩትን 60 ፓርቲዎችና ኣሟልታችኋል ተብለው በምርጫ ኮሚሽን ህጋዊ እውቅና ያገኙትን 46 ፓርቲዎችን ጋብዞ መቀሌ ላይ ለስብሰባ ተቀመጠ። በሰረቀው መዋእለ ንዋይ ቀጥሮ ማእከላይ መንግስቱን ለማዳከም መምርያ ሰጥቶ እንዳሰማራቸው የቅርብ ጊዜ ትዝታ ነው። እነዚህ ፓርቲዎች ከህዝባቸው ተሰርቆ እነሱን በቀጠረው ገንዘብ ድንብርብር ኣሉ።በሩቅ ገጠር የሚገኝ ድምጹ ተስምቱ የማውቅ የገዛ ህዝባቸውን እርስ በእርሱ ኣጋጭተው ስያናቁቱና ለኣመታት ጥሮ ግሮ ያፈራውን ቤት ንብረቱን ኣወደሙ። ከ2,000,000 ህዝብ በላይ በመጠለያ እንደ እቃ ሲታሸግ ዴሞክራትዋ ኣሜሪካና ተከታዮችዋ ተፈጥሮ በለገሰላቸው ኣይንና ጀሮ ብቻ ሳይሆን ዘመን ባፈራው ቴክኖሎጂ እያዩና እየሰሙ ጭጭ ማለቱን ለምን መረጡ? በስደት የቆዩት የፓለቲካ ፓርቲ ቅሬቱች ገና እዛው ኣሜሪካ መሽገዋል። ከግብጽና ዲያስፖራውን ኣደናግረው ባገኙት ገንዘብ ለ24 ሰዓት ኤለክትሪክ ባለው ምርጥ ቤት እየሰፈሩ ጥዋት ትኩስ ወተት ከማክዶናልጋ ቆርሰው ነገር ሲጋግሩ ውለው ማታ ማታ ወያኔ በተከራየለችው የተሌቪዥን ጣብያ ህዝብን ከህዝብ የሚጋጭ የውሸት እንጀራ ህዝባቸውን ሲጋብዙ ተስተውለዋል። ለዚህ ኣስነዋሪ ድርጊት ድምጸ ተኣቅቦ ኣድርጎ የቆየው የኣሜሪካ መንግስት የለውጥ ኣመራሮ ብዛት ያላቸው ፕሮጀክቶች ተጀመሩ፣ ተጨረሱ፣ ተመርቁ፣ የኣባይ ግድብ ለረጅም ጊዜ ሲጓተት ቆይቶ በኣጭር ጊዜ ኣንደኛ ሙሌቱን ፈጽሞ ለሁለተኛና የመጨረሻ ሙሌቱ ቀናት ብቻ መቅረቱን ሲሰሙ ነገሩ ከቁጥጥራቸው እየወጣ መሆኑን ኣወቁ። ይህኔ ነው የጥፋት ሬሞት ኮንትሮላቸውን ዋሽንግተን ሆነው ጫን ያደረጉዋት። ቅጠረኛው ደሞ ህዝቡንና ታሪኩን ወደ ጎን ትቶ በ3/4 የኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት ላይ ጨለማን ተገን ኣርጎ ጦርነት ከፈተ። ኤርትራን በሚሳይል ደበደበ። በእንዲህ ኣይነቱ ጡት ነካሽ ከሃዲ ቡድን ላይ የኢትዮጵያ ህዝብና መንግስት ተገቢውን እርምጃ ወሰደ። የኤርትራ ህዝብና መንግስት ከሞትና ምርኮ ተርፈው ወደ ኤርትራ ድንበር የመጡትን እንዴት እንደተቀበልቸው በሰራዊቱ ቢነገር ይሻላል ብየ ትቸዋለሁ። የተዛባ ጥናት ላይ ተመርኩዘው እርምጃውን የወሰዱት ወያኔዎችና ትእዛዙን ያስተላለፉት ኣሜሪካኖች ነገሩ “የጎጡን ኣወርድ ብላ የብብቷን ጣለች” ሆነባቸው። ምክንያቱም ኢትዮጵያን ኣተራምሰው ለመቆጣጠር የወጣው ውጥን ከሽፎ ትግራይንም ኣጧትና።
  3. የለውጥ ኣመራሮ ሃይልና ዛቻ የኢትዮጵያን ህዝብ በተፈጥሮ ሀብታም እያለ ግን ድሃ ያደረገውን ሰበብ ጠንቅቆ ያወቀ ይመስላል። መደመር፣ ኣንድነትና ይቅርታ እያለ ላለፉት 3 ዓመታት ሌተ ቀን ሲዘምር እየሰማን ነው። ስለሆነም ነው ከኣራቱም ማእዘን የተውጣጡ እናቶች፣ መቀሌ ድረስ ሄደው በዚያ ልክስክስ ሃሳቡን በልሳኑ መገለጽ እማይችለው የትግራይ ክልል ም/ፕረዚደንት ፊት ተንበርክከው ደም እያለቀሱ ለሰላም፣ እርቅና ኣንድነት ሲለምኑ የሰጠውን ትእቢት የተሞላበትን መልስ ሰምተነዋል። ይህ ኣልበቃ ብሎ የሃይማኖት ኣባቶች፣ ምሁራንና ለኢትዮጵያና ህዝቧ ትልቅ ውለታ በፈጸሙ ቀላል እማይባል ቁጥር ባላቸው የሰላም ቡድን በተመሳሳይ መንገድ ወያኔ የተጠናወተውን ሰይጣናዊ ኣመለካከት ለማርገብ ሞክረዋል። ግን ትእቢተኛው ቡድን ባለው ኣቅም ሳይሆን በቀጠሩት ሃይል ተማምኖ ለ27 ዓመታት ያዙኝ ልቀቁኝ ሲል እንዳልቆየ በ15 ቀን ደብዛው ጠፋ። እነ ኣቦይ ስብሃትና ቀላል እማይባሉ ምርኮኞች ለኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት ገጸ በረከት ኣስረክቦ፣ እነ ኣባይ ጸሃየ፣ ስዩም መስፍን፣ ኣስመላሽ፣ ጌታቸው ኣሰፋንና ሌሎችን ለዘላለም ኣሰናብቶ መደበቅያ ዋሻ ፍለጋ ላይ ታች ሲል እያየን ነው። በዚህ ኣጋጣሚ ሁላችንም የሰው ልጆች በእናታችን ማህጸን ከ 9 ወር ቆይታ በኋላ ወደዚች ኣለም እንደመጣን ግልጽ ነው። እናት ልጆችዋን ኣንዱን ከሌላ ለመለየት የመረጠችውን ስም ትሰጣለች። ኢትዮጵያም እንደ እናት የወለደቻቸውን ወንድማማቶች ኣንዱን ከሌላው ለመለየት ከንባታ፣ ወላይታ፣ ጉራጌ፣ ትግሬ፣ ኦሮሞ፣ ኣማራ፣ ወዘት ብላ 84 ስም ሰጥታ ትዳር መስርተው እሚኖርበትን ከባቢ ኣከፋፈለች። ከሁሉም ኣንዱ ጋጠወጥ ሁኖ በሌሎች ልጆችዋ ላይ ኣመጽ ግድያ ብማዘውተር የሃዘን ቁራኛ ሆና እንድትኖር የሚያደርገውን መርገምዋ ኣይቀሬ ነው። ስለዚህ ወንድሞች ባህላችሁን፣ ወጋችሁን ጠብቃችሁ የዕድሜ ባለጸጎችን፣ የሃይማኖት መሪዎችንና የወላጆቻችሁን ምክር መስማትና ማክበር የሞራል ግዴታ መሆኑን መዘንጋት የለባችሁም። ካልሆነ ግን የትግራይ ህዝብ ሳይሆን በትግራይ የበቀለው ወያኔ ባሳየው ትእቢት የወላጅ እናቱ እርግማን ደርሶበት በኣጭር ጊዜ መቀጨቱ መልካም ማስረጃ ይሆናል ብየ ኣምናለሁ። 
  4. ኣሜሪካንና ቅጥረኛ የኣካባቢ ሃገራትን ሞራልና ብርታት የሰጠው ቀደም ብሎ በተሓህትና ኦነግ ተዘርቶ በቅሎ ጊዜውን ጨርሶ መርገፍ ላይ የነበረው ቋንቋንና ብሄርን መሰረት ያደረገው ኣስተሳሰብ ነው። ኣንድነት፣ ፍቕር፣ ይቕርታ በሚሉ ኣዲስ ትውልድ ተገፍትሮ እመቃብር ኣፋፍ ላይ ደርሷል። ግን ኣሁንም ይህ ያረጀ ያፈጀ ኣስተሳሰብ የተጠናወታቸው ቅሪቶች ኣዲሱ የለውጥ ኣመራር ያመቻቸውን ነጻ መድረክ ተጠቅመው በኣጭር ጊዜ 106 ጫጭቶች ተፈለፈሉ። ነገሩ “በእንቅርት ላይ ጀሮ ደግፍ” ሆነ። የኢትዮጵያ ህዝብ ሃብትና ንብረት ለመመዝበር የነበረው መግብያ ቀዳዳ ወደ 106 ኣሽቀበ። ኣሰፍሰፈው ለሚጠባበቁት ኣማጽያን ማንን ኣቅፈው ማንን ለመጣል ሰፊ ኣማራጭ ተመቻቸላቸው። እድሉን ስላገኙ መንገዱ በየትኛው የጎረቤት ኣገር ይመቻል ፍለጋ ላይ ሲራወጡ እያየን ነው።

እስኪ መለስ ብለን ኢትዮጵያ ያለፈችበትን ጠመዝማዛ መንገድ እንፈትሽ።

ኣሜሪካ ከሃይለስላሴ እስከ የኢህኣደግ ዘመነ መንግስት ህዝቡን ረግጠው በረሃብና ኣላስፈላጊ ጦርነት ውስጥ ማግደው ኣመድ ድቤውን ሲያጠጡት ስርኣታቱን ኣይዞህ ብለው ሲያበረታቱ መቆየታቸውን ተባለ ተብሎ ሲወራ ሳይሆን እማሃልና ጥግ ሆነን ስናየው ቆይተናል። ሃይለስላሴን በስልጣን ለማስቀጠል ብዙ ላይ ታች ኣሉ ኣልሆነላቸውም። ቀጥለውም ደርግ ውድቀቱ ተቃርቦ ሲንገዳገድ ጦረተኛ ፕረዚደንቶችዋን ልካ እንዴት ከናይሮቢ ኬንያ ወደ ኣትላንታ ኣሜሪካ መጨረሻ ላይ ለንደን እንግሊዝ ኣገር ተደራዳሪዎችን ይዛ እያለች ኣስመራ ላይና ኣዲስ ኣበባ ላይ የግጥሚያውን ፍጻሜ የሚያበስር ፊስካ ተነፋ። ድርድሩ ላይ የነበሩት የደርግ ኣባላት እዛው ቀሩ፣ መንግስቱና መሰሎቹ ደሞ ፈረጠጡ።

የወያኔ ኢህኣደግ ገና ትግል ላይ እያለ ሶቭየትንና ቻይናን ረግጦ ርእዮት ኣለሙን የኣልባንያ ዜግነት እስከ ሰጠበት ወቅት ሲከታተሉት ቆዩና ኣባብለው ቅጥረኛ ሰራዊታቸው ለማድረግ ጊዜ ኣልወሰደባቸውም። 5 ከመቶ የኢትዮጵያ ህዝብ ቁጥር የያዘው ወያኔ ጠ/ሚኒስተር፣ ውጭ ጉዳይ፣ መከላከያ፣ ጤና፣ የብሄራዊ ባንክ ፕረዚደንት፣ የውሃና ኤነርጂ ሚኒስተር ወዘተ በኣገር ደረጃ ሁሉንም ቁልፍ ቦታዎች ተቆጣጠሩ። በኣጭር ጊዜ የወያኔ ሚኒስተሮችና ጀነራሎች እዚህም እዛም በወር ከ36 ሺ እስከ 120 ሺ የሚከራዩ ቤቶች ባለቤት ለመሆን በቁ። ከዚህ የተረፈውን ደሞ በተላያዩ የኣለም ባንኮች ሲከምሩ የኣሜሪካ መንግስትና ባላስልጣናት እንደነ ሱዛን ራይት ለሚደረገው ስርቆት ጠበቃ ቆመው ወያኔንና ኣመራሩን እንዴት ያቆላምጡት እንደነበር ማን ይረሳዋል።

በተለያዩ ኣከባቢዎች ህዝቡ እነዚህን የቀን ጅቦች ማሳደድ ጀመረ ግን መሳርያው ከድንጋይ ያላለፈ ስለነበር ኣጋኣዚ ክ/ጦር እና ሌሎች በብዛት ወጣቱን መረሸን እለታዊ ስራቸው ሆነ። የሰብኣዊ መብት ጠበቃ ነን ባዮች ኣሜሪካውያን ግን ኣሁንም ኣይተው እንዳላዩ ጭጭ ኣሉ። በመጨረሻ የህዝቡ ግፊት ስለበረታ በኢህኣደግ ውስጥም ቀን ይጠብቅ የነበረው የለውጥ ሃይል ወያኔን ገፍትሮ ስልጣኑን ተቆጣጠረ። ይህኔ ወያኔ ጓዘን ጠቅሎ መቀሌ ገባ። በኢህኣደግ ዘመነ መንግስት ወንጀል የፈጸሙ ወደ ሕግ እንዲቀርቡ ጥሪ ቢላክላቸው ኣሻፈረኝ ኣሉ። መቀሌ ላይ መሽገው ተላላኪ ፍለጋ ላይታች ኣሉ። ለዚህም በስልጣን ያለውን መንግስት ወደ ጎን ትተው ኣሁን በውድድር ያሉትንና የተባረሩትን የፓለቲካ ፓርቲዋች መቀሌ ላይ ለስብሰባ ጠሩ። በባለ 5 ኮኮብ ሆቴል ተኝተው ወያኔ ያዘጋጀላቸውን ድግስ ተቋድሰው ተልእኳቸውን በማስታወሻ ደብተራቸው ጽፈው ወደየ መጡበት ኣካባቢ ተመለሱ። ለሁለትኛ ጊዜ ኣዲስ ኣበባን ጨምሮ በትላልቅ ክተሞች ስንት ሃብትና ጉልበት የፈሰሰበት የንጹሃን ዜጎች ንብረት ወደመ፣ በሚልዮን የሚቆጠር ህዝብ ተፈናቀለ። መንግስት የህግ የበላይነት ማስከበር ብቃት የለውም ተብሎ የድራማው ከያኔ እና ተዋናዮቹ መንጋጋቸው እስኪፈርስ ሳቁ ተደሰቱ።

በተፈጠረው ግጭት ዳግም እማይመለስ የብዙ ንጹሃን ዜጎች ሂወት ጠፋ፣ ንብረት ወደመ ግን 4ኪሎ ቤተመንግስት የመቆጣጠር ህልማቸው በነነ። ይህ ኣጋጣሚ ኣንድ የኣባቶቻችን የትግርኛ ምሳሌ ኣስታወሰኝ “በትሪ ሓቅስ ትቐጥን እምበር ኣይትስበርን” ትርጉም “የእውነት በትር ትቀጭጫለች እንጂ ኣትሰበርም” ነው። ይህ ኣልሁን ሲላቸው ፓርቲዋቹ በመርፊ ቀዳዳ የለውጥ ሃይሉን ድክመት ፍለጋ ላይ ተጠምዶ። ይህን ተከትሎ በመጪው ምርጫ የሚወዳደሩ ፓርቲዎች የሚያደርጉትን ክርክር በኢቲቪ፣ ፋናና ዋልታ ስከታተል የሰማሁት ስድብና ብሽሽቅ ገረመኝ። በክርክሩ መድረክ፡ ከተመረጡ መንግስታቸው የሚከተለውን ኣቋም ሲዘርዝሩ ኣንዱ ከሌላው ኮርጆ መጣ እንዳይባሉ ይመስል ኣንዱ ቁ.1 ብሎ የጠቀሰውን ሌላኛው ቁ.3 ሌላው 5ኛ ሌላው 10ኛ ብለው ኣስቀምጠውታል። ኣንዱ ያነበበውን ሌላው ሲደግመው እንጂ ኣዲስ ኣሳብ ይዞ የመጣ ኣልሰማሁም። ከሰማሁት የኣንድ ፓርቲን ልጥቀስ።

የኢዜማው ም/ፕረዚደንት የማእከላዊውን መንግስት ድክመት ኣገኘሁ ብሎ ሲተርክ የሰማሁት እንደሚከተለው ነበር። “በተለያዩ ኣካባቢዎች ሰዎች በብዛት እየሞቱ ገዥው ፓርቲ እልቂቱን ከምንም ስላልቆጠረው ሃገራዊ ባንዴራውን ዝቅ ብሎ እንዲውለበለብ ኣላደረገም።”

መቸ ይህ ብቻ ስም ጠቅሶ ኣምባገነን ብሎ ሲሳደብ ተሰማ። ለመሆኑ ባንዴራው ዝቅ ብሎ መውለብለቡ ለተፈናቃዩ ምሳ፣ እራት፣ መድሃኒትና መጠለያ ይሆነዋል ብሎ ነው? ለምንስ ይሆን ማእከላይ መንግስት ህዝቡን ኣስተባብሮ በኣጭር ጊዜ ኣስፈላጊውን እርዳታ ማድረሱንና ሁኔታውን ኣረጋግቶ ተፈናቃዮችን ወደየ ቒያቸው መመለሱን እንደቁምነገር ለማየት የተሳነው? መልሱን ለኢትዮጵያ ህዝብ እተዋለሁ።

ስንበት ብሎ ደሞ ፕረዚዳንቱ (ኢዜማ) ብልጽግና የኣዲስ ኣበባ ህዝብ ድምጽ ለመግዛት በከተማዋ በሕገ ወጥ መንገድ ተይዘው የነበሩ መኖርያ ቤቶች እየስጠ ነው ሲል ተሰማ። ከጥቂት ጊዜ በፊት ይህ ድርጅት በኣዲስ ኣበባ በጥናት ስለ ኣገኛቸው በመቶዎች እሚቆጠሩ ብሕገ ወጥ የተያዙ ቤቶች እያሉ ደሃው ህዝብ በቤት እጦት እየተሰቃየ መሆኑን ጋዜጣዊ መግለጫ ሲሰጥ ተሰምቶ ነበር። እነዚህ በሕገ ወጥ መንገድ ተይዘው የነበሩ ቤቶች ለምን ዓይነት የህብረተሰብ ክፍል እንደተሰጡ ግን ሳይጠቅስ ሸፈፍ ብሎ ኣለፈው። እኔን የገረመኝ ከተማ መስተዳድሩ (ብልጽግና) ኣንዲ በሕገ ወጥ መንገድ የተያዙት ቤቶች በችግር ላይ ላሉ የህብረተሰብ ክፍል ኣልተፈታም ሲሉ ሰንብተው በሌላ ግዜ ከተማ ኣስተዳድሩ በሕገ ወጥ መንገድ ተይዘው የነበሩትን ቤቶች ለስንኩላንና በዝቅተኛ የኑሮ ጀረጃ ላሉ በሚሰጥበት ጊዜ ደሞ የምርጫ ድምጽ ለመሸመት ቤቶችን እየቸረቸረ ነው ብሎ መክሰስ የጤነኛና ለህዝብ የቆመ የፓለቲካ ፓርቲ ኣስተሳሰብ ነው ለማለት ይከብዳል።

ከትላንት ወዲያ በኢህኣፓ፣ ትላንት በግንቦት 7 ስም ለ44 ኣመታት በስደት ካገር ኣገር ሲዋልል ቆይቶ ኣገር እንዲገባ ቀጠልያ መብራት ሲበራለት ኣገር ገብቶ ዛሬ ኢዜማ ብሎ ስም ቀይሮ በልጁ ላይ ይህን ያህል ተንኮል መሽረብ የት ለመድረስ ይሆን? ምክንያቱም ብርሃኑንና የቅርብ ጓደኛው እንዳርጋቸው ጽጌ ውጤት ኣልባ ኢህኣፓን መስርተው ትግል ጀመርን በሚሉበት ጊዜ (1966) ኣሁን እነሱን ከእስር ቤትና ከስደት ኣገር እንዲገቡ ያስቻለውን ለውጥ የመራው ወጣት ያኔ ገና ወደዚች ኣለም ብቅ ኣላለም ነበር።

እንዳርጋቸው ጽጌ “ትውልድ እንዳይደናገር እኛም እንናገር” በሚል ርእስ ለህትመት ያበቃውን መጽሓፍ ኣንብቤያለሁ። በቤተ መንግስት ቅጥር ግቢ ካደገ ቤተሰብ የተፈጠረ መሆኑንም ገልጾልናል። በሌላ በኩል በኢህኣፓ ምስረታ በሹፌርነት ተቀጥሮ ለኢትዮጵያ ህዝብ ነጻነት ትግሉን እንደጀመረ ለማስረዳት ሞክሯል። ግን ገና ኣሁንም የሃይለስላሴ ወራሪ ባህሪ እንደተጠናወተው በኤርትራ ላይ የኢትዮጵያ ህዝብ ኣሰብን ለመያዝ ዱላ እንዲያነሳ የሚገፋፋ የመጽሓፉ ኣንድ ኣካል በሆነው “የኤርትራ ዱላ” በሚል ርእስ ላይ የጻፈው በግልጽ ኣሳይቶናል። ይህ ወረራ በሚፈጸምበት ጊዜ በሁለቱ ወገን የሚከፈለው መስዋእትነት ዝቅተኛ እንዲሆን ተመኝቶልናል፣ ምክንያቱም እሱ ነገር ለኩሶ በሩቅ ሆኖ የማራገብ ልምድ ስላለው። እንደኔ የመጽሓፉን ርእስ “ትውልድ እንዲደናገር እኔም ልናገር” ቢለው የተሻለ ይሆንለት ነበር። ምክንያቱም ለ30 ዓመት በተከፈለው መስዋእትነትና በኣለም ኣቀፍ ህግ መሰረት እውቅና ባገኘች ልኡላዊት ኣገር ላይ ጦርነት መቀስቀስ ትውልድን እንዲደናገር ከማድረግ ሌላ ምን ስም ይሰጠዋል።

ሌላው ኣስገራሚ ነገር የኢትዮጵያ መንግስት ማንኛውም ኢትዮጵያዊ በማንኛውም የፓለቲካ ድርጅት ኣባል ለመሆን ድርብ ዜግነት ሊኖረው ኣይገባም የሚል ህግ ኣለው። ይሄኔ ነው እንዳርጋቸው ከፓለቲካ እንቅስቃሴ ራሴን ኣግልያለሁ ብሎ ኣዜማን የተወ መስሎ ባለው ድርብ ዜግነት ወደ እንግሊዝ ኣገር የበረረው። የኢዜማ የውጭ ጉዳይ ኣስፈጻሚ ሆኖ ስራውን በመቀጠል ላይ ይገኛል። ለዚህ ግልጽ ማስረጃ ሰውየው ቀዋሚ ቦታ ስለሌለው ቀዋሚ ስራ ይዞ እሚያገኘው ቀዋሚ ገቢ የለውም። ታድያ ይህን ከኣህጉር ወደ ኣህጉር በቀጣይ የሚያደርገውን ጉዞ ለኣየር ትኬት፣ ሆቴልና ሌላም ሌላም ወጪ ማን ነው የሚሸፍነው? መልሱን ለግዜ እንተወው።

በኣጠቃላይ ኣሁን ኣለን ብለው ድምጻቸውን በማሰማት ላይ ያሉ የፓለቲካ ድርጅቶች ከመጠን በላይ መብዛታቸው ለኢትዮጵያ ህዝብ ጤና የሚሰጥ ኣይደለም። “ኣንድነት ሃይል ነው” የተባለው ኣለምክንያት ኣልነበረም። በኣንድ የፓለቲካ ፓርቲ ላይ ተሰብሰቡ ማሌቴ ግን ኣይደለም። ግፋ ቢል ሁለትና ሶስት ላይ ተደምራችሁ ለውድድር ብትቀርቡ ህዝቡን ኣንድነትና ጥቅሙን ማስተማሩ ላይ ገና ስትጀምሩ የማስተማር ድርሻችሁን በመወጣት በቀላሉ ለማስረዳት ትችሉ ነበር ብየ ነው። ካልሆነ ግን እናት ኣክስት፣ ኣዲስ ትውልድ ኣሮጌ ትውልድ፣ ባላደራ፣ ህብር ወዘተ ተብሎ መነጣጠሉ ግን ውድቀታችሁን መርጣችሁ ወደ ውድድሩ መግባታችሁን ከወዲሁ ብታውቁና ለሽንፈታችሁ እንደ ትላንቱ ትራምፕ ምክንያት ፈጥራችሁ ህዝቡን ላልተፈለገ ግጭት እንዳትዳርጉ እማጸናለሁ። ምክንያቱም “ከወደቁ ኋላ መንፈራገጥ ትርፉ መላላጥ ነውና።”

ፈጣሪ የኣከባቢውን ህዝብ ይጠብቅ!!

Must read

ጅግንነት ኤርትራውያንን ኢትዮጵያውያንን ኣብ 50 ዓመቱ

ዓርቢ 08 ታሕሳስ 1972፡ ቅድሚ 50 ዓመት፡ ኣብ መዓርፎ ነፈርቲ ኣዲስ ኣበባ ሓደ ምንጋሩ ዘጸግም ፍጻሜ ተኻየደ። ኣብ ክሊ ዕድመ 24- 28 ዝርከቡ ሰለስተ ኤርትራውያንን ኣርባዕተ ኢትዮጵያውያንን ንነፋሪት ንመገዲ ኣየር ክጨውዩ ተበገሱ። እቶም ክልተ ተማሃሮ ዩኒቨርሲቲ፡ እቶም ኣርባዕተ ገሊኦም ትምህርቶም ዛዚሞም ኣብ ስራሕ ዝተዋፈሩ...

ናጽነት ከቢድ ዋጋ ከፊልካ ይመጽእ፣ ከቢድ ዋጋ እንዳኸፈልካ ድማ ይዕቀብ

"ዝሞተ ነይክሰስ ኣብ ሰማይ ነይሕረስ" እኳ እንተኾነ፣ ስቕ ዘየብል ክትዕዘብ እንከለኻ ስቕታ ኣይትመርጽን። "ኣዲኣ ገዲፋስ ሓትንኣ ትናፍቕ" ከምዝብሃል ብምኽንያት ሞት ንግስቲ ዓባይ ብርጣንያ ልዕልቲ ኤልሳቤጥ፣ መንግስቲ ኬንያ ናይ ሰለስተ መዓልታት ሃገራዊ ሓዘን ኣዊጁ ክትስምዕ ዘደንጹው እዩ። መቸም ብሰንኪ ምስፍሕፋሕን ጎበጣን ንግስነት ዓባይ ብርጣንያ ኣብ ሃገራትን...

ሓንጎል፡ ሓሞት፡ ደም

ኣብዚ ቀረባ ቕነ ንሓጺር እዋን ምስቲ ኣዝየ ዘድንቖ መራሒ ተራኺበ ከዕልል ዕድል ረኺበ ነይረ።  ምልክት ቃልሲ ኤርትራውያን ንናጽነትን ኣርካን ኣቦ ሰውራን ውሩይ መራሒ እዩ። ብትሑት ኣነባብራኡን ምቕሉልነቱን ዝፍለጥ ሰብ እዩ። ኣብ መዓልታዊ ህይወቱ ዝገብሮ ንጥፈታት ካብ ዝኾነ ተራ ዜጋ ዝተፈልየ ኣይኮነን። ከም ተራ ዜጋ ይኽደን፡ ኣብ መንጎ ህዝቡ ኣብ ንእሽቶ ገዛ ይነብር፡ ከምቲ ልምዲ ሕብረተሰብና ድማ ኣብ ኩሉ ማሕበራዊ ንጥፈታት ከም ዝኾነ ተራ ዜጋ ይሳተፍ። ኣብ መላእ ሃገር ብናጽነት ዝንቀሳቐስ፡ ምስ ህዝቡ ሕዉስ መራሒ...

Shida Friendship Forum

On the occasion of Eritrea’s 31st Independence Celebrations, Shida Media will live stream a panel discussion on Saturday 21st of May at 9AM LA time, 12PM NY time, 6PM Berlin time and 7PM Asmara and Addis Ababa time. The distinguished panelists are: Alemseged Tesfai -...

More articles

1 COMMENT

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

- Advertisement -spot_img

እዋናዊ ዜና