ሲጀመር- አሁን በዓለምችን ላይ ላሉት ታላላቅ ችግሮች ሁሉ የመነሻ ምንጭ ምዕራባውያን ናቸው ብንል የተጋነነ አይደለም።ሲቀጥል- ምዕራባውያን ያላቸውን የሓይል ሚዛን ለመጠበቅ፣ አሁን የሚታዩትን ችግሮች ባሉብት ማስቀጠል፣ ለወደፊትም ተጨማሪ ችግሮችን መፍጠርና ችግሮቹን ማስተዳደር፣ የሚለው ፖሊሲያቸው ለዘመናት የሰሩበትና አሁንም በዋነኛነት የሚያራምዱት ነው።
ምንም እንኳን የችግሩ ምንጮች ምዕራባውያኖቹ ይሁኑ እንጂ፣ ከሁለተኛው የዓለም ጦርነት በህኀላ እራሳቸው በቀጥታ ሳይሆን በተዘዋዋራ በሃገር-በቀል አሽከሮቻቸው አማካኝነት ነው ይህን እኩይ ፖሊሲያቸውን ሲያስፈጽሙ የቆዩት።አንዳንዴም እራሳቸው በቀጥታ በመግባት የማይስማሟቸውን መንግስታትን ገልብጠው፣ መሪዎቻቸውን ገድለው ወይም አስወግደው ሲያበቁ፣ እንደተለመደው በዴሞክራሲና በሰብአዊ መብቶች አላክው ይሳለቁብናል።
የሚደንቅ እና የሚገርም ነው። ሰውን በባርነት እንደ እቃ የሸጡ እና የለወጡ፣ አህዛብን እንደ ዲኖሳውርየር ከዓለም ገጽ ያጠፉ፣ በዘርኝነት የጥቁሮችን አእምሮ ከዝንጀሮ ጋር ያወዳደሩ፣ የሌሎችን መሬቶች በቀኝ ግዛት ወረው በመያዝ አህዛብን ያጎሳቆሉና ሃብቶቻቸውን የዘረፉ፣ እጆቻቸው በደም የበሰበሱ ምዕራባውያን፣ ተገልብጠው ስለ ሰብአዊነትና ስለ ዴሞክራሲ ለእኛ ሲሰኩን ይውላሉ። ብዙዎችም እውነት መስሏቸው አፋቸውን ከፍተው ይሰሟቸዋል።
እናም እንደ ኤርትራ ያሉ ጠንካራ፤ የሞራል ልእልና ያላቸው፣ የምዕራባውያንን ስነልቦና ጠንቅቀው የሚያቁ፣ ሃብታቸውን የማያስነኩ፣ አሽከርነትን የሚጠየፉ ሃገራት በምዕሪባውያን የሚወርድባቸው የተቀናጁ ጥቃቶችን መገመት አያዳግትም።
ብዙዎች ሃገራት ጥቃቱን መቋቋም ያቅታቸውና እጅ ይሰጣሉ። ኤርትራን ግን እጅ ማሰጠት አልተቻለም። ለወደፊቱም አይቻልም።ለምን ቢባል ኤርትራ በነበሩት እውነተኛ ታሪኮች እንጂ በትርክቶች የማታምን፣ ወጣቷን የምትገነባ፣ በራስዋ የምትተማመን፣ ሰርቶ በመለወጥ እንጂ በረድኤት የማታምን፣ ልመናን የምትጠየፍ፣ ሃብቷን መቆጣጠር የምትችልና የራስዋን ፖሊሲዎች የምትቀርጽ ሃገር ስለሆነች።
ብዙዎች ከላይ የተጠቀሱት በውንድሞቻችን ሃገር በኢትዮጵያ የሉም። ምክንያቱም ከዚ ቀደም በአተኩሮ ስላልተሰራባቸው።
አሁን በስልጣን ላይ ያለው የአብይ አህመድ መንግስት ኢትዮጵያን የምዕራባውያን ሳይሆን የኢትዮጵያውን ማድረግ እንደሚቻል በደንብ ገብቶታል። ይቻላልም!
ይኸው ኤርትራ ህያው ምስክር ነች።
ጥያቄው የአብይ መንግስት የምዕራባውያንን ሁለንተናዊ ጫና ተቋቁሞ ይሻገረዋል ወይ? የሚለው ነው።
ኢትዮጵያና ኢትዮጵያውያን ከመልካም ግረቤታቸው ከኤርትራና ከኤርትራውያን ብዙ መማር ይችላሉ።
አብይ ህዝቡን በማንቃት ረገድ ትልቅ ስራዎችን ከሰራ፣ ህዝቡሙ ትርጉም ከሌለው ትርክት እና የዘር ፖለቲካ ወጥቶ፣ ነቅቶ፣ ጥቅሙ ተረድቶትና የባለቤትነት ስሜትን ተላብሶ የአብይን መንግስት ከደገፈው፣ ኢትዮጵያም እንደ ኤርትራ የራሱዋ ባለቤት ትሆናለች።
ምዕራባዊያኖቹም ሌሎች ያልነቁባቸው ወይም ነቅተው ድፍረት ያጡት ጋር ሆደው የአዞ እምባቸውን ማፍሰሳቸውን ይቀጥላሉ።