የአውሮፓ ህብረት ቡችላው የማፊያ ቡድን ህውሓት በሰሜኑ እዝ ላይ ጥቃት ከሰንዝረ በኋላም እንኳን፣ ቡድኑ የፈጸማቸውን እጅግ መጥፎ ድርጊቶች ጆሮ ዳባ ልበስ በማለት ችላ ብሎ ሲያልፉት ስንታዘብ ሰንብተናል።ይልቁንስ የአውሮፓ ህብረት የኢትዮጵያን መንግስት አንዳንዴ በመገሰጽ፣ አንዳንዴ ረድኤት በመከልከል፣ አንዳንዴም ለማስፈራራት በመሞከር ወደ ውይይት አስገዶ ለመግፋት የተቻለውን ሁሉ ጥረት አደረጏል፡፡አሁን ላይ የአውሮፓ ህብረት እንደለመደው ስለ ሰብአዊ ቀውስ ስጋት ትምህርት እየሰጠን ነው፡፡
ህወሓት በሁሉም የኢትዮጵያ አካባቢዎች እና በኤርትራ ህዝብ ላይ የዘር ማጥፋት እና ሁሉንም ዓይነት ግፍ ሲፈጽም የአውሮፓ ህብረት የት ነበር?
የአውሮፓ ህብረት ያኔ ምንም ሰብአዊ ቀውስ አይታየውም ነበር፣ ቢታየው አንስቶ አያውቅም፡፡
ይልቁንስ ለ27 ዓመታት በግብረ-ሽበራና ሌሎች የውሸት ምክንያቶች ሽፋን የገንዘብና ሌሎች ሁለንተናዊ ከፍተኛ ድጋፎችን፣ ለስራ አስፈጻሚውና አሽከሩ ህወሓት ያደረገ ነበር፡፡
የመላው የአፍሪካ ቀንድ ሕዝቦች የህወሓትን መጥፋት ሲያከብሩና የተስፋ ንፋስ መተንፈስ ሲጀምሩ፣ በአንጻሩ የአውሮፓ ህብረት እና በአጠቃላይ የምዕራባውያኑ ጫጫታ ለምን?
ለምን ህወሓትን መመለስ እንደሚፈልጉ ባይገርመንም ይደንቀናል፡፡
ወያነ ከስድስት ጫማ በታች ተቀብራለች!
የአውሮፓ ህብረት በሰብአዊ ቀውስ አሳቦ በትግራ ክልል ሙሉ እንቅስቃሴ እንዲፈቀድለት ጥሪ በተደጋጋሚ እያቀረበ ነው። ለትግራይ ክልል ለሰብአዊ ትግሮች ከኢትዮጵያውያ ብላይ ሰብአዊነት ይሰማኛል እያለም የአዞ እምባ እያፈሰሰ እው።
ዳሩ ግን ጩኸቱ ከሰብአዊ ቀውስ ችግሮች ጋስ የተያያዘ ሳይሆን፣ ፍላግታቸው ትግራይ ውስጥ የቀሩትን በጣም ጥቂት የወያነ መሪዎችን ማዳን ነው።