ኢዜማ ትግራይን አስመልክቶ መግለጫ አውጥቷል።
መግለጫው መግለጫ ሳይሆን፣ ኢዜማ በመጪው ምርጫ የትግራ ህዝብን ቀልብ በመሳብ የምርጫ ድምጽ ለማግኘት የተሰራ ርካሽ የፖለቲካ ዝሙት ነው።
ማን ጠርቶሽ አቤት አልሽ ይላሉ አበው።
የሚገርመው ደግሞ ኢዜማ በዚህ ርካሽ የፖለቲካ ዝሙታችው ኤርትራን በወያኔ ዘመን እንደተለመደው፣ ኤርትራን የሰይጣናዊ ስራዎች ምንጭ የሆነች ሃገር አርገው ለመቅረጽ መሞክራቸው ነው።
የኢዜማ ርካሽ ጨዋታ በዚህ ዘመን አይሰራም!
የኢትዮጵያ ህዝብ የኤርትራን ህዝብ እውነተኛ ምስል እና ማንነት በሚገባ ተረድቶታል።
በመጀመሪያ የኤርትራን ህዝብ፣ ሰራዊትና መንግስት ምን ያህል ጨዋ እንደሆኑ የኢዜማ መሪዎችና ተከታዬቻቸው በደንብ ጠንቅቀው ያውቃሉ።
ምክንያቱም የኢዜማ ዋና ጸሐፊ ፖሮፌሰር ብርሃኑ ጨለመ እና ተከታዮቻቸው ምድር እንደ ገሐነብ ብሆነችባቸው በዛ ክፉ ዘመን፣ ኤርትራ መስዋእት ከፍላ፣ ጨዋነትን አስተምራ፣ ገነት ሆና ብርሃኑንና ተከታዮቹን ለዚህ ያበቃችው ስለሆነች።
በመቀጠልም የወያኔ ጁንታ የሰሜን እዝ አባላትን በተኙበት ረሽና፣ ገሚሱን ወደ ኤርትራ አባራ፣ የተረፋትንም አስራ፣ 80% የሚጠጋውን የኢትዮጵያ ጦር መሳርያውን በቁጥጥር ስር አውላ ኢትዮጵያን የማፍረስ ስራዋን ስትጀምር፣ የኤርትራው መንግስትና ሰራዊት ሁኔታውን አንብቦ፣ ሩጫዋን ቀጭቶ፣ ያባረረቻቸውን የኢትዮጵያን ሰራዊት አባላት አደራጅቶና አስታጥቆ ሃሳቧን በአጭር እንዲቀር የአንበሳውን ድርሻ አስተዋጽኦ ባያደርግ ኖሮ፣ ብርሃኑ ጨለመና የኢዜማ ጀሌዎቹ አሁን ኢትዮጵያ የምትባል ሃገር አትኖራቸውም ነበር።
ዳሩ ግን በትምህርት ካተማሩት ይልቅ በትርክት የሰሙትን ተረት እውነት አርገው በሚያዩ ሰዎች በሚመራ ኢዜማ፣ የፖለቲካ ዝሙት እንጂ ሌላ አይጠበቅም። በዚህ መግለጫም ይህንኑ ነው ያሳዩን።
ስለዚህ ነው ደግሞ የአመራር ብቃት ያሳየውን፣ ወያኔን ድባቅ የመታውን፣ የኤትራን መልካም ጉርብትና የሚፈልገውንና ኤርትራ በቀጠናው ያላትን ተጽእኖ ፈጣሪነት የተረዳውን፣ የአብይ አህመድ የብልጽግናን መንግስት የመፎካከር አቅም የሌላቸው።
ኢዜማ መዝሙርና አሉባልታ እንጂ ስራና ክውንነት ምኑም ሆነው አያውቁም።