ጅንታው ኢትዮጵያን በጦርነት በማመስና ቀጠናውን በጦርንት በማቀጣጠል ከመሸገበት የትግራይ ክልል ወደ ስልጣን የመመለስ ህልሙን ጋህድ ለማድረግ ረዘም ላለ ግዜ ሁለንተናዊ የጦር ዝግቱን ጨርሶ የኢትዮጵያን የሰሜን እዝ ሰራዊትን በተኛበት ረሽኖና ገድሎ በኢትዮጵያና በኤርትራ ላይ ጦርነት ጀመረ።
የኢትዮጵያ መከላከያ ሰሪዊት በደረሰበት ክህደትና ቅፅበታዊ ድብደባ ሁኔታዎችን የመቆጣጠር ቁመና ላይ ስላልንበረና የመከላከል አቅምም ስላልነበው፤ እንዲሁም ጅንታው ኤርትራን በሮኬት በመደብደብ ሽብር መንዛት ላይ ስለነበረ፣ ጀግናው ህዝባዊ የኤርትራ መከላከያ ሰራዊት ሃገሩን ለመከላከል፣ ኢትዮጵያን ከመፍረስ ለማዳን፣ ጅንታውን ላአንዴና ለመጨረሻ ግዜ ለመቅበርና አካባቢውን ለማረጋጋት ወደ ኢትዮጵያ ለመግባት ተገደደ።
እስከ ዛሬ ዓለት ድረስ ግዴታውን በሚገባ በመፈጸም ሃገሩን ከጥቃት ተከላክሎ፣ ኢትዮጵያን ከመፍረስ አድኖ፣ ጅንታውን ቀብሮ እነሆ ዛሬ በወግ ተልእኮውን በጀግነት ፈጽሞ ወደ ሃገሩ መመለስ ጀምሮአል።
ክብርና ሞገስ ለጀግናውና ለባለውለታው የኤርትራ መከላከያ ሰራዊት!