19 C
Asmara
Thursday, September 14, 2023

የግብረ-ሰይጣን NGO ድርጅቶች ስውር አላማ

ዘመኑ ግብረ-ሰናይ የረድኤት ድርጅቶች እንደ ጉድ የበዙበት ዘመን ነው።
እነዚህ የእርዳታ ድርጅቶች መንግስታውያን እንዳልሆኑ፣ ከመንግስታት ተጽእኖ ነጻ እንደሆኑ፣ የሰብአዊ መብቶችና ሰብአዊ ቀውሶች ከሌሎች በላይ እነርሱን እንደሚመለከታችው ነው አእምሮአችን እየተነገረው ይምናድገው።
ለዚህም ነው በዚህ መልኩ ሰፊው ጭቁኑ የዓለም ህዝብ የሚያያቸው። አፍሪካ ላይ እማ እንደ ፈጣሪም የሚታዩበት ስፍራዎች ጥቂት አይደሉም።
እነዚህን ድርጅቶች ግን ከጀርባ ሆነው የሚያሽከረክሯቸው እና የሚቆጣጠሯቸ ምዕራባውያን መንግስታትና ታላላቅ የምዕራባውያን የግል የንግድ ኩባንያዎች ናቸው።
የግብረ- ሰናይ ድርጅቶቹ ጉዳይ በጣም ጥልቅ እና ውስብስብ የሆነ የንግድና የጭቆና መረብ ነው።
ምዕራባውያን በየሃገሮቻቸው ያሏቸውን ሰብአዊ ችግሮች ወደጎን ትተው፣ ለዘመናት ባዳከሟቸው ደሃ ሃገሮች ላይ በረድኤት ስም መረባረብ አንድምታው ምንድነው? ምንስ ጥቅም ቢኖራቸው ነው?
ነገሩ ከወዲህ ነው፣
በመጀመርያ ለዘመናት በችግር ያደቀቋቸውን ሃገራት በዘር፣ በሃይማኖት፣ በጎሳ፣ በመሬትና በሌሎች የተለያዩ ምክንያቶች እርስ በራሳቸው የማናቆት ስውር ሴራዎችን ይጠነስሳሉ።
በመቀጠልም ውስጣዊ አድርባይ ሎሌዎችን በመቅጠር እኩይ ስራቸውን ያራምዳሉ፣ ያስፈጽማሉ።
ከዚያም ቀውሱ እንዲባባስ በጭድ ላይ እሳት በመልቀቅ ሰብአዊ ቀውሶቹ እንዲባባሱ ጠንክረው ይሰራሉ።
በዚህ ግዜ የችግሩን መንስኤ በሚገባ ለመረዳት ፋታ የማያገኙት እነኝህ ችግሩ የተፈጠረባቸው ሃገራት፣ ያላሰቡትና ቅፆበታዊ ችግር ስለሚሆንባቸው፣ በደከመ አቅማቸው ችግሩን ለመቆጣጠር ላይ እና ታች ሲሉ የችግሩ ዋና አለቆች፣ ሴረኞቹ ምዕራባዊያን ቅዱሳን መስለው ረድኤት ይዘው ይከሰታሉ።
በችግራችን ጊዜ ደረሱልን፣ እኛን ሊያግዙና ምንም ላይጠቀሙ ውቅያኖስ አቋርጠው መጡልን፤ የሚሉ የዋሆች ብዙዎች ናቸው።
ላይጠቀሙ ምናቸው ስለሆንን ነው ላይ እና ታች የሚሉልን? ብለው የሚጠይቁት ግን ጥቂቶች ናቸው።
መገንዘብ ያለብን
መጀመሪያ ለህዝብ ግልጽ መሆን የሚገባው እነዚ በግብረ-ሰናይ የሚታወቁ ግን ደግሞ ግብረ-ሰይጣናዊ ስራዎችን የሚያራምዱ ድርጅቶች፣ ሲሰጡ እንጂ በስውር ሲዘርፉ የማይታዩ፣ በምዕራባውያን መንግስታት እና ትላላቅ ኩባንያዎች ባለቤትነት ስር የሚተዳደሩት ድርጅቶች መሆናቸውን ነው።
ሲቀጥል የእነዚ አደገኛ ድርጅቶች ዋነኛ አላማ ቀውስ ውስጥ የከተቷቸው ሃገራትን መንግስታዊ ተቋማት ሽባ በማድረግ፣
በረድኤት ስም ህዝቦችን ከአምራችነት ወደ ተመጽዋትነት በመቀየር፣ በመጨረሻም በተጠና መልኩ የመንግስታቱን ተቋማት በራሳቸው ተቋማት በመተካት የሃገራትን ሃብትና ንብረቶች መቆጣጠርና መዝረፍ ነው።
ይህ ነው ደግሞ አዲሱ የቅኝ ገዢዎች ስልት ወይም Neocolonialism ተብሎ የሚጠራው።
በዚህ ረገድ ከኤርትራ በቀር ሁሉም የአፍሪካ ሃገራት ሃብታቸውን ሊቆጣጠሩ የማይችሉ የአዲሱ ቀኝ ግዛት ሰለባዎች ናቸው ቢባል የተጋነነ አይሆንም።
ይህ ማለት ግን መፍትሄ የለውም ማለት አይደለም። እንደ ኢትዬጵያ ያሉ ዘግይተው የባነኑና ነገሩን መስመር ለማስያዝ እየሞሩ ያሉ ሃገራት ጥቂት አይደሉም።
ለዚህም ነው ደግሞ ምዕራባዊያን ኢትዮጵያ የግብረ-ሰይጣን ድርጅቶች ትግራይ ውስጥ እንዳይገቡ ከለከለች በሚል ጩኸት የተቀናጀ ጥቃታቸውን የተከፈቱባት።
ኤርትራ የግብረ-ሰይጣኖችን አጀንዳ በማለዳው በመረዳት አይደለም እነሱ፣ የእነሱ ወፍ እንኳን በኤርትራ ምድር ዝር እንዳትል ካደረገች እነሆ 3 አስርት ዓመታት ሊቆጠሩ ነው። ለዚህም ትልቅ መስዋእት ከፍላለች እየከፈለችም ነው።
በኤርትራ ላይ የሞከሩት ሁሉ አልተሳካም!
ለምን ቢባል፣ ኤርትራ የራሷ ባለቤት የሆነች፣ ማንም መጥቶ ጣቱን የማይቀስርባት፣ ከብድራቸው የጸዳች አንድና ብቸኛ አፍሪካዊት ነጻ ሃገር ስለሆነች።
እንግዲህ ከላይ በጠቀስናቸው ነጥቦች መነጽር ነው የወቅቱን የነጮች ጩኸት የምናየው።
የወቅቱ ጩኸት
ምንም እንኳን ህግ ለማስከበር በተካሆደው ውጊያ ችግሩ ይስፋ እንጂ በትግራይ ክልል ከውግያው በፊትም ርሃብ ነበር።
ወያኔ ያስተዳድራት የነበረችው ትግራይ በሴፍቲ-ኔት(safety net) አይደለም እንዴ የምግብ ኮታዋን ትዘጋ የነበረው?
ታዲያ ያኔ ያሁኑ ጩኸት ለምን ኣልተሰማም?
ያኔና አሁን ያለው የትግራይህዝብ አንድ አይደለም እንዴ?
ልምንስ ጩኸቱና ጫጫታው አሁን በዛ?
የኢትዮጲያ ህዝብ ልብ በል!
ኢትዮጲያ ብዙ ሃብት ያላት፣ በብዛት ወጣቶች የሚኖሩባት ሃገር ናት።
መሰሪ ባእዳውያንን ከማሀልህ አስውግደህ፣ በኣንድ ላይ መቆም ካልቻልክ ይበሉሀል!
ነገሮችን ተርድተህ፣ ነቅተህ በኣንድ ላይ ከመቆም ግን ነገሮች ይቀየራሉ።
አይደለም ኢትዮጵያን አውሮፓውያንንም መመገብ አቅም ያለት ሃገር ነው ተንተርሰህ ያለኸው።
ረድኤት ከመጠበቅና ስለ ረድኤት ከማውራት አቅምህን አቀናጅተህ ተነስ! ታጠቅ! ስራ!
ሌሎቹ አማራጮች ሁሉ ከንቱ ናቸው።
ውጤታቸው ደግሞ ከዚህ በፊት ታይቷል። ከባርነትንና ከተንበርካኪነት አልፈው ያመጡት ፋይዳ የለም።

Must read

ጅግንነት ኤርትራውያንን ኢትዮጵያውያንን ኣብ 50 ዓመቱ

ዓርቢ 08 ታሕሳስ 1972፡ ቅድሚ 50 ዓመት፡ ኣብ መዓርፎ ነፈርቲ ኣዲስ ኣበባ ሓደ ምንጋሩ ዘጸግም ፍጻሜ ተኻየደ። ኣብ ክሊ ዕድመ 24- 28 ዝርከቡ ሰለስተ ኤርትራውያንን ኣርባዕተ ኢትዮጵያውያንን ንነፋሪት ንመገዲ ኣየር ክጨውዩ ተበገሱ። እቶም ክልተ ተማሃሮ ዩኒቨርሲቲ፡ እቶም ኣርባዕተ ገሊኦም ትምህርቶም ዛዚሞም ኣብ ስራሕ ዝተዋፈሩ...

ናጽነት ከቢድ ዋጋ ከፊልካ ይመጽእ፣ ከቢድ ዋጋ እንዳኸፈልካ ድማ ይዕቀብ

"ዝሞተ ነይክሰስ ኣብ ሰማይ ነይሕረስ" እኳ እንተኾነ፣ ስቕ ዘየብል ክትዕዘብ እንከለኻ ስቕታ ኣይትመርጽን። "ኣዲኣ ገዲፋስ ሓትንኣ ትናፍቕ" ከምዝብሃል ብምኽንያት ሞት ንግስቲ ዓባይ ብርጣንያ ልዕልቲ ኤልሳቤጥ፣ መንግስቲ ኬንያ ናይ ሰለስተ መዓልታት ሃገራዊ ሓዘን ኣዊጁ ክትስምዕ ዘደንጹው እዩ። መቸም ብሰንኪ ምስፍሕፋሕን ጎበጣን ንግስነት ዓባይ ብርጣንያ ኣብ ሃገራትን...

ሓንጎል፡ ሓሞት፡ ደም

ኣብዚ ቀረባ ቕነ ንሓጺር እዋን ምስቲ ኣዝየ ዘድንቖ መራሒ ተራኺበ ከዕልል ዕድል ረኺበ ነይረ።  ምልክት ቃልሲ ኤርትራውያን ንናጽነትን ኣርካን ኣቦ ሰውራን ውሩይ መራሒ እዩ። ብትሑት ኣነባብራኡን ምቕሉልነቱን ዝፍለጥ ሰብ እዩ። ኣብ መዓልታዊ ህይወቱ ዝገብሮ ንጥፈታት ካብ ዝኾነ ተራ ዜጋ ዝተፈልየ ኣይኮነን። ከም ተራ ዜጋ ይኽደን፡ ኣብ መንጎ ህዝቡ ኣብ ንእሽቶ ገዛ ይነብር፡ ከምቲ ልምዲ ሕብረተሰብና ድማ ኣብ ኩሉ ማሕበራዊ ንጥፈታት ከም ዝኾነ ተራ ዜጋ ይሳተፍ። ኣብ መላእ ሃገር ብናጽነት ዝንቀሳቐስ፡ ምስ ህዝቡ ሕዉስ መራሒ...

Shida Friendship Forum

On the occasion of Eritrea’s 31st Independence Celebrations, Shida Media will live stream a panel discussion on Saturday 21st of May at 9AM LA time, 12PM NY time, 6PM Berlin time and 7PM Asmara and Addis Ababa time. The distinguished panelists are: Alemseged Tesfai -...

More articles

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

- Advertisement -spot_img

እዋናዊ ዜና