የሟቿ ጁንታ የዲያስፖራ እና የሃገር ውስጥ ርዝራዦች፣ እንደ ጣኦት የሚያመልኳትና ጠፍጥፋ የሰራቻቸው ጁንታውያን የስነ-ልቦና እናታቸው በህልም እንኳን ሊታያቸው በማይችል ሁኔት ከጠፋች ወዲህ በከባድ ሃዘን፣ ድንጋጤና ቀውስ ውስጥ ይገኛሉ።
እንደ ፈጣሪ የሚያምኗት ውሸታሟ ጣኦታቸው ላትመለስ ከተሸኘች እነሆ ወራትን መቁጠር ጀምረናል።
እነኝህ ልባቸው በከቦድ ሃዘን የተሰበረው ውድ ልጆቿ ቀብሯ ላይ እንኳን እንዲሳተፉም ሆነ ሃዘናቸውን በወግ ለመቀመጥ ኣልፈቀድንላቸውም።
ከእንቅልፋቸው ቀስቅሰው ነው ውዷ የውሸት ልእልት እናታቸው በክፉ መጥፋቷን የተነራቸው።
እንግዲህ እነኝህ ርዝራዦቿ በእደዚህ ድብልቅልቅ ባለ የስነ ኣእምሮ ቀውስ ውስጥ ሆነው ነው ሓዘናቸውን፣ ብስጭታቸውን፣ የልብ ስብራታቸውንና የስነልቦና ሞታቸውን ለማስታገስ ዉድ እናታቸው እንዳስተማረቻቸው በውሸት ኤርትን መወንጀሉን ስራዬ ብለው የተያያዙት። በሉ እንግዲህ ግፉበት ይመቻችሁ!
ኤርትራ ባትገባና ባተባበር ኖሮ፣ ሶማልያ ባትገባና ባተባበር፣ ዓረብ ሃገራትም ባይገቡ ኖሮ፣ የዓለም መንግስታትም ዝም ባይሉ ኖሮ፤ እኛ ተራራውን አንቀጥቃጮቹ ትግራዎትን የሚያሸንፈን ባልተገኘ ነበር የሚለው አዲሱ ዘፈናቸው በጣም ተመችቶኛል።
ኤርትራ አልገባችም! ብትገባስ?
-
የዓይናችሁ ቀለም አላማረንም ብላ ከ80ሺ በላይ ኤርትራውያንን በግፍ ከኢትዮጵያ አባራ ንብረታቸው የዘረፈች ህወሓት።
-
በባድመ አሳባ ውጊያ በመክፈት የ19ሺ ኤርትራውያን ወጣቶችን ሕይወት ያስቀሰፈችው ህወሓት።
-
የድንበሩን የፍርድ ውሳኔ አልቀበም አሻፈረኝ ብላ የኤርትራን ልኡላዊ መሬት በጌቶቿ አይዞሽ ባይነት አለቅም ያለችው ህወሓት።
-
የአካባቢውን መንግስታት በማስተባበርና በተካህነችበት ውሸት በማታለል የኤርትራን መንግስት ለማግለል ሳተኛ ያደረችው ህወሓት።
-
በጌቶቿ ቡራኬና በእርሷ እብሪት ላለፉት 20 ዓመታት ኤርትራን በቀጣይ በመውጋት እና በውጊያ ለማጥመድ በመሞከር ከጠዋት እስከ ማታ ተመጣጣኝ ምላሽ ሰጥተናል እያለች ያቅራራችው ህወሓት።
-
ሶማሊያ ውስጥ እሷ በኢትዮጵያ ስም ሕገወጥ ንግድና ዘረፋ ለማካሆድ፣ ጌቶቿ ደሞ የሱማሊያን የባሕር ሃብት ለመዝረፍ ሲገቡ ኤርትራ በመቃወሟ ውሸት ጠፍጥፈው ኤርትራ ላይ ማዕቀቡ እንዲጣል አልቅሳ ጌቶቿን ለምና፣ ጌቶቿ ማዕቀብ ሲጥሉብን በደስታና በእብራት የፈነደቀችው ህወሓት።
-
የህወሓት ተደጋጋሚ ውጊያዎችና የጌቶቿ ማዕቀቡ በኤርትራ በፈጠረው የኢኮኖሚ ቀውስ ወጣቶቻችን ሲሰደዱ፣ በየበረሃው ሲንገላቱና ሲሞቱ የተሳለቀችው ህወሓት።
-
ዓላማችን የኤርትራን መንግስት መገልበጥ ነው ብላ በአደባባይ የጮኅችው ህወሓት።
-
ከለውጡ ወዲህም የተለያዩ ችግሮችን በመፍጠርና የኢትዮጵይ ሰራዊት ከኤርትራ ልኡላዊ መሬት እንዳይወጣ በመከልከል ሰላሙ እንዳይጥናከር ያሴረችው ህወሓት።
-
የሰሜኑን እዝ የኢትዮጵይ ወታደሮች በትኙበት በጥይት ደብድባ የገደለች እና የተረፉትንም እራቁትቸውን ከተደፈረው የኤርትራ ልኡላዊ መሬት እስከ ነጻው የኤርትራ መሬት ኣሳድዳ የገደለች ህወሓት።
-
በተደጋጋሚ ኤርትራ ላይ የሮኬት ድብደባ ያደረገችው ህወሓት።
-
ኤርትራ ተዋጊ ሰራዊት የላትም፣ ወጣቶቿን ያጣች የአንድ ቀን ቁርስችን ናት። እኛን ለማጥፉት እንዳትስብ ካሰበች ደግሞ መኖሯ ያበቃል ብላ በአደባባይ ስትቀደደድ የነበረችው ህወሓት።
-
አስመራም ትሁን አዲስ አበባ ከኛ የሮኬት ቁጥጥር ውጪ አይደሉም ብላ ስትፎክር የከረመችው ህወሓት።
ትናንት ካለኛ ማን አለ ውጊያ አዋቂ፣ ጦርነት የባህል ጨዋታችን ነው! እያለች እንዳልፎከረች ከጦርነቱ አንድ ሳምንት አስቀድማም ኤርትራ ተዋጊ ወጣት ሰራዊት የላትም ስትለን የነበረችው ጃንዳ በማግቱ ኤርትራ 18 ክፍለ ጦር ይዛ በትግራይ ተከሰተች ብላ እርፍ (በትንሹ 64 000 ሺ የኤርትራ ወታደር ማለት ነው)።
ይህም አልበቃ ብሏት ሳይውሉ ሳያድሩ ደግሞ 10 ሺ የኤርትራ ሰራዊት ማርከናል ብላ ጡሩምባ መንፋት ጀመረች።ጉድ ነው ዘንድሮ ጎበዝ
እና አሁን ምን ይጠበስ?
ያሁሉ ሽለላ፣ ቀረርቶ እና ፉከራ ተረሳና አሁን ደግሞ የኤርትራ ሰራዊት ወጋን፣ ገደለን .. እያሉ በአውሮጳው እና በአሜሪካዉ ቀዝቃዛ ክረምት የመኪና መንገድ ላይ እየተንፈራፈሩ ንዴታቸውን የማቀዘቅዝና ሓዘናቸውን በጩኅት የመግለጽ ህግመንግስታዊ መብታቸው ስለሆነ አይከለከሉም።እኛም የእነርሱን ጥሩ የኮሜዲ ተውኔት እያየን ጮቤ እየረገጥንነው ። አቦ ይመቻችሁ ቀጥሉበት እንዳታቋርጡት ተስማምቶናል። ኤርትራ በህውሓት ቀብር የመሳተፍ ሙሉ መብት አላት። እንዲያውም ደብረጽዮን ነው የኤትራን ሰራዊት በወግ የጋበዘው። ህውሓታውያን እውነቱን ተቀበሉ የኢትዮጵይ መከላከያ ሰራዊት ልክ አስገብቷቹሃል።
ኤርትራ ካገባችም እሰየው!!
እቺ ጉደኛ ጁንታ የሰሜን እዝ አባላትን ገድላ፣ ገሚሱን ወደ ኤርትራ አባራ፣ የተረፋትንም አስራ፣ 80% የሚጠጋ ይጦር መሳርያውን በቁጥጥር ስር አውላ ነገሮችን ህወሓት ስሌት ማስኬድ ስትጀምር ጀግናው የኤርትራው ሰራዊት ሁኔታውን እንብቦ፣ ሩጫዋን ቀጭቶ፣ ያባረረችውን የኢትዮጵይን ሰራዊት አደራጅቶና አስታጥቆ ሃሳቧን በአጭር እንዲቀር አስተዋጽኦ ባያደርግ ኖሮ ኢትዮጵያውያ እና ኢትዮጵያውያን አሁን በምን ሁኔት ውስጥ ይገኙ እንደነበር መገመት ቀላል ነው።