አዲስ ምእራፍ!

0
72
TESFAYE GEBREAB
እነሆ! በአፍሪቃ ቀንድ አዲስ ምእራፍ እየተከፈተ ይመስላል። በተለይ ግን በኢትዮጵያ እና በኤርትራ መካከል።
ማለትም የወያኔ ተከታታይ ተንኮል ለዘለአለሙ አከተመለት። ኮሮና ቫይረስ የከፋ ጉዳት ሳያደርስ ክትባቱ ተገኘ።
 
እንግዲህ ምን ቀረ?
አሰብ ወደብ እና ምጽዋዕ ወደብ ስራ እንደሚጀምሩ ጥያቄ የለውም። በአማራ ክልል እና በኤርትራ መካከል የተገነባው ተንኮለኛ አጥር መፍረሱ ለውጡ ካመጣቸው ድሎች አንዱ ነው።
የትግራይ ወጣቶች ቀስ በቀስ ከሰመመናቸው ሲንቁ፣ ወያኔ ካሳደረባቸው ሙስናዊ ጥቅም ተላቀው ከኢትዮጵያውያን ወንድሞቻቸው እና ከኤርትራውያን ጎረቤቶቻቸው ጋር በመከባበር ላይ የተመሰረተ ግንኙነት ያዳብራሉ። ይህ የማይቀር እውነት ነው።
ርግጥ ነው፣ ኤርትራ እና ኢትዮጵያ የመጪው ዘመን ባለተስፋ አገራት እንደሚሆኑ አያጠራጥርም። የኢትዮጵያ 6ኛው ምርጫ ምንም እንኩዋ የተሟላ ሊሆን እንደማይችል ግልጽ ቢሆንም፣ የርዳታ ሰጪ አገራትን አፍ ለመዝጋት ኢትዮጵያ የይስሙላ ምርጫ ማድረግ ግድ ሆኖባታል። ዞረም ቀረ የመጪው አምስት አመታት የኢትዮጵያ መሪ አብይ እንደሚሆን ግልጽ ሆኗል።

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here