ዘመኑ ግብረ-ሰናይ የረድኤት ድርጅቶች እንደ ጉድ የበዙበት ዘመን ነው። እነዚህ የእርዳታ ድርጅቶች መንግስታውያን እንዳልሆኑ፣ ከመንግስታት ተጽእኖ ነጻ እንደሆኑ፣ የሰብአዊ መብቶችና ሰብአዊ ቀውሶች ከሌሎች በላይ እነርሱን እንደሚመለከታችው ነው አእምሮአችን እየተነገረው ይምናድገው። ለዚህም ነው በዚህ መልኩ ሰፊው ጭቁኑ የዓለም ህዝብ የሚያያቸው። አፍሪካ ላይ እማ እንደ ፈጣሪም የሚታዩበት ስፍራዎች ጥቂት አይደሉም።እነዚህን ድርጅቶች ግን ከጀርባ ሆነው የሚያሽከረክሯቸው እና የሚቆጣጠሯቸ ምዕራባውያን መንግስታትና ታላላቅ የምዕራባውያን የግል የንግድ ኩባንያዎች ናቸው።የግብረ- ሰናይ ድርጅቶቹ ጉዳይ በጣም ጥልቅ እና ውስብስብ የሆነ የንግድና የጭቆና መረብ ነው። ምዕራባውያን በየሃገሮቻቸው ያሏቸውን ሰብአዊ ችግሮች ወደጎን ትተው፣ ለዘመናት ባዳከሟቸው ደሃ ሃገሮች ላይ በረድኤት ስም መረባረብ አንድምታው ምንድነው? ምንስ ጥቅም ቢኖራቸው ነው?
ነገሩ ከወዲህ ነው፣
በመጀመርያ ለዘመናት በችግር ያደቀቋቸውን ሃገራት በዘር፣ በሃይማኖት፣ በጎሳ፣ በመሬትና በሌሎች የተለያዩ ምክንያቶች እርስ በራሳቸው የማናቆት ስውር ሴራዎችን ይጠነስሳሉ። በመቀጠልም ውስጣዊ አድርባይ ሎሌዎችን በመቅጠር እኩይ ስራቸውን ያራምዳሉ፣ ያስፈጽማሉ። ከዚያም ቀውሱ እንዲባባስ በጭድ ላይ እሳት በመልቀቅ ሰብአዊ ቀውሶቹ እንዲባባሱ ጠንክረው ይሰራሉ።በዚህ ግዜ የችግሩን መንስኤ በሚገባ ለመረዳት ፋታ የማያገኙት እነኝህ ችግሩ የተፈጠረባቸው ሃገራት፣ ያላሰቡትና ቅፆበታዊ ችግር ስለሚሆንባቸው፣ በደከመ አቅማቸው ችግሩን ለመቆጣጠር ላይ እና ታች ሲሉ የችግሩ ዋና አለቆች፣ ሴረኞቹ ምዕራባዊያን ቅዱሳን መስለው ረድኤት ይዘው ይከሰታሉ።
በችግራችን ጊዜ ደረሱልን፣ እኛን ሊያግዙና ምንም ላይጠቀሙ ውቅያኖስ አቋርጠው መጡልን፤ የሚሉ የዋሆች ብዙዎች ናቸው። ላይጠቀሙ ምናቸው ስለሆንን ነው ላይ እና ታች የሚሉልን? ብለው የሚጠይቁት ግን ጥቂቶች ናቸው።
መገንዘብ ያለብን
ጀመሪያ ለህዝብ ግልጽ መሆን የሚገባው እነዚ በግብረ-ሰናይ የሚታወቁ ግን ደግሞ ግብረ-ሰይጣናዊ ስራዎችን የሚያራምዱ ድርጅቶች፣ ሲሰጡ እንጂ በስውር ሲዘርፉ የማይታዩ፣ በምዕራባውያን መንግስታት እና ትላላቅ ኩባንያዎች ባለቤትነት ስር የሚተዳደሩት ድርጅቶች መሆናቸውን ነው። ሲቀጥል የእነዚ አደገኛ ድርጅቶች ዋነኛ አላማ ቀውስ ውስጥ የከተቷቸው ሃገራትን መንግስታዊ ተቋማት ሽባ በማድረግ፣በረድኤት ስም ህዝቦችን ከአምራችነት ወደ ተመጽዋትነት በመቀየር፣ በመጨረሻም በተጠና መልኩ የመንግስታቱን ተቋማት በራሳቸው ተቋማት በመተካት የሃገራትን ሃብትና ንብረቶች መቆጣጠርና መዝረፍ ነው።
ይህ ነው ደግሞ አዲሱ የቅኝ ገዢዎች ስልት ወይም Neocolonialism ተብሎ የሚጠራው።
በዚህ ረገድ ከኤርትራ በቀር ሁሉም የአፍሪካ ሃገራት ሃብታቸውን ሊቆጣጠሩ የማይችሉ የአዲሱ ቀኝ ግዛት ሰለባዎች ናቸው ቢባል የተጋነነ አይሆንም።ይህ ማለት ግን መፍትሄ የለውም ማለት አይደለም። እንደ ኢትዬጵያ ያሉ ዘግይተው የባነኑና ነገሩን መስመር ለማስያዝ እየሞሩ ያሉ ሃገራት ጥቂት አይደሉም። ለዚህም ነው ደግሞ ምዕራባዊያን ኢትዮጵያ የግብረ-ሰይጣን ድርጅቶች ትግራይ ውስጥ እንዳይገቡ ከለከለች በሚል ጩኸት የተቀናጀ ጥቃታቸውን የተከፈቱባት።ኤርትራ የግብረ-ሰይጣኖችን አጀንዳ በማለዳው በመረዳት አይደለም እነሱ፣ የእነሱ ወፍ እንኳን በኤርትራ ምድር ዝር እንዳትል ካደረገች እነሆ 3 አስርት ዓመታት ሊቆጠሩ ነው። ለዚህም ትልቅ መስዋእት ከፍላለች እየከፈለችም ነው።በኤርትራ ላይ የሞከሩት ሁሉ አልተሳካም!ለምን ቢባል፣ ኤርትራ የራሷ ባለቤት የሆነች፣ ማንም መጥቶ ጣቱን የማይቀስርባት፣ ከብድራቸው የጸዳች አንድና ብቸኛ አፍሪካዊት ነጻ ሃገር ስለሆነች።
እንግዲህ ከላይ በጠቀስናቸው ነጥቦች መነጽር ነው የወቅቱን የነጮች ጩኸት የምናየው።
የወቅቱ ጩኸት
ምንም እንኳን ህግ ለማስከበር በተካሆደው ውጊያ ችግሩ ይስፋ እንጂ በትግራይ ክልል ከውግያው በፊትም ርሃብ ነበር።ወያኔ ያስተዳድራት የነበረችው ትግራይ በሴፍቲ-ኔት(safety net) አይደለም እንዴ የምግብ ኮታዋን ትዘጋ የነበረው? ታዲያ ያኔ ያሁኑ ጩኸት ለምን ኣልተሰማም? ያኔና አሁን ያለው የትግራይህዝብ አንድ አይደለም እንዴ? ልምንስ ጩኸቱና ጫጫታው አሁን በዛ?
የኢትዮጲያ ህዝብ ልብ በል!
ኢትዮጲያ ብዙ ሃብት ያላት፣ በብዛት ወጣቶች የሚኖሩባት ሃገር ናት።መሰሪ ባእዳውያንን ከማሀልህ አስውግደህ፣ በኣንድ ላይ መቆም ካልቻልክ ይበሉሀል!ነገሮችን ተርድተህ፣ ነቅተህ በኣንድ ላይ ከመቆም ግን ነገሮች ይቀየራሉ።አይደለም ኢትዮጵያን አውሮፓውያንንም መመገብ አቅም ያለት ሃገር ነው ተንተርሰህ ያለኸው። ረድኤት ከመጠበቅና ስለ ረድኤት ከማውራት አቅምህን አቀናጅተህ ተነስ! ታጠቅ! ስራ! ሌሎቹ አማራጮች ሁሉ ከንቱ ናቸው።ውጤታቸው ደግሞ ከዚህ በፊት ታይቷል። ከባርነትንና ከተንበርካኪነት አልፈው ያመጡት ፋይዳ የለም።